በእኔ ላይ ያለህ አላማ
Benie Lay Yaleh Alama
2001 · ትራክ 5 · 4:52 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና
እኔም ላክብርህ በዜማ ስለወጣሁ ከጨለማ
በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና
እኔም ላክብርህ በዜማ ስለገባኝ የአንተ አላማ
ቁጥር 1 · Verse 1
አላማህ በእኔ ላይ ፍቅር ሆኖ እንጂ
አይገባም ነበር ልትሆነኝ ወዳጅ
ይህንን እያሰብኩ ሁሌ አመልክሃለሁ
ጠላቴ እየሰማ ዘምርልሃለሁ (፫x)
አዝማች · Chorus
በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና
እኔም ላክብርህ በዜማ ስለወጣሁ ከጨለማ
በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና
እኔም ላክብርህ በዜማ ስለገባኝ የአንተ አላማ
ቁጥር 2 · Verse 2
የሰላም ሃሳብ ነው የምታስብልኝ
ፍጻሜና ተስፋ እንዲሆንልኝ
እኔም ከፈቃድህ በፍፁም አልወጣም
ከአንተ ተለይቼ መኖር አልመኝም (፫x)
አዝማች · Chorus
በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና
እኔም ላክብርህ በዜማ ስለወጣሁ ከጨለማ
በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና
እኔም ላክብርህ በዜማ ስለገባኝ የአንተ አላማ
ቁጥር 3 · Verse 3
በሃጥያቴ ምክንያት ሞት ተፈርዶብኝ
ለሲኦል ለእሳት የታጨሁ ሳለሁኝ
አምላኬ ግን ፍቅርህ ለእኔ ስለበዛ
ከሞት አመለጥኩኝ ስለሆንከኝ ቤዛ (፫x)
አዝማች · Chorus
በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና
እኔም ላክብርህ በዜማ ስለወጣሁ ከጨለማ
በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና
እኔም ላክብርህ በዜማ ስለገባኝ የአንተ አላማ
ቁጥር 4 · Verse 4
ፍቅርህን በሞትህ ስለገለጽክልኝ
የዘለዓለም ሕይወት በነጻ አገኘሁኝ
ክብሬን እያየሁ በአንተ ዘንድ ያለውን
አዜምልሃለሁ እጅግ ደስ እያለኝ (፪x)
አዜምልሃለሁ በአንተ ደስ እያለኝ
አዝማች · Chorus
በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና
እኔም ላክብርህ በዜማ ስለወጣሁ ከጨለማ
በእኔ ላይ ያለህ አላማ አምላኬ ፍቅር ነውና
እኔም ላክብርህ በዜማ ስለገባኝ የአንተ አላማ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ