ተመስገን
Temesgen
2001 · ትራክ 7 · 8:14 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ተመስገን ጌታዬ ተመስገን
ተመስገን አምላኬ ተመስገን (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እንደ እናት በጀርባ አዝለህ አሳደግከኝ
ክፉም እንዳይነካኝ በእጅግ ሰወርከኝ
ውበት ደም ግባቴ ሞገሴ ሆንክልኝ
እኔም ዝም አልልም ለአንተ አዜማለሁኝ
አዝማች · Chorus
ተመስገን ጌታዬ ተመስገን
ተመስገን አምላኬ ተመስገን (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሁልጊዜ ሳስበው ለኔ ያደረከውን
ቃላቶች ያጥሩኛል አንተን ለማመስገን
በብዙ ሃጥያቴ ዘወትር ሳስቸግርህ
በፊትህ አልጣልከኝም አምላኬ አቆመኝ ምህረትህ
አዝማች · Chorus
ተመስገን ጌታዬ ተመስገን
ተመስገን አምላኬ ተመስገን (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ብዙ ማይታለፍ ተራራ ሸለቆ
አምላኬ አንተ ነህ ያሳለፍከኝ እኮ
እኔስ የአንተ ውለታ ከልቤ አይጠፋም
ሁሌ አዜመዋለሁ ላፍታ ዝም አልልም
አዝማች · Chorus
ተመስገን ጌታዬ ተመስገን
ተመስገን አምላኬ ተመስገን (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ለዓለም ለሚመጣው ትውልድ አወራለሁ
ያደረክልኝን እመሰክራለሁ
ብዙ ዘመናትን ወራት ዓመታትን
በእራሴ አይደለም ያለፍኩት በአንተ ነው ተመስገን
አዝማች · Chorus
ተመስገን ጌታዬ ተመስገን
ተመስገን አምላኬ ተመስገን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ