በአንተ ደስ ይለኛል
Be Ante Des Yelegnal
2001 · ትራክ 8 · 6:26 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ክብር የሚገባው ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
ስግደት የሚገባው ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
ሙገሳ የሚገባው ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
አምልኮ የሚገባው ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
አዝማች · Chorus
በአንተ ደስ ይለኛል ሃሴትም አደርጋለሁ
የምሥጋና ቅኔን በፊትህ እቀኛለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሞትን ያሸነፈ ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
ሰይጣንን የረታ ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
ጸሎትን የሚሰማ ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
እንቆቅልሽ ፈቺ ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
አዝማች · Chorus
በአንተ ደስ ይለኛል ሃሴትም አደርጋለሁ
የምሥጋና ቅኔን በፊትህ እቀኛለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የምስኪኑ ወዳጅ ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
የደሃ አደግ አባት ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
ታማኝ ሚስጥረኛ ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
በጽድቅ የተሞላ ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
አዝማች · Chorus
በአንተ ደስ ይለኛል ሃሴትም አደርጋለሁ
የምሥጋና ቅኔን በፊትህ እቀኛለሁ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እውነተኛ ጌታ ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
እውነተኛ አምላክ ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
እውነተኛ ወዳጅ ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
እውነተኝ አባት ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
አዝማች · Chorus
በአንተ ደስ ይለኛል ሃሴትም አደርጋለሁ
የምሥጋና ቅኔን በፊትህ እቀኛለሁ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ሙገሳ የሚገባው ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
ሽብሸባ የሚገባው ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
ጭብጨባ የሚገባው ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
አምልኮ የሚገባው ማነው ቢባል
ከአንተ በቀር የለም (፪x)
አዝማች · Chorus
በአንተ ደስ ይለኛል ሃሴትም አደርጋለሁ
የምሥጋና ቅኔን በፊትህ እቀኛለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ