ሌላ ቃላት የለኝም
Liela Qalat Yelegnem
2001 · ትራክ 3 · 5:56 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ክብሬን ሁሉ ጥዬ ለአንተ እሰግዳለሁ
የሽቶዬን ብልቃጥ በፊትህ እሰብራለሁ
እግርህ ስር ወድቄ እገዛልሃለሁ
ላከበርከኝ ጌታ ይህም ሲያንስህ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ሌላ ቃላት የለኝም አንተን የማከብርበት
ግን አንዲያው ተመስገን ልበልህ በሰጠኸኝ አንደበት (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በምንስ ጀምሬ በምን ልጨርሰው
ጌታ ውለታህን በምን ቃል ልግለጸው
እንዲያው ዝም ብዬ ክብርን እሰጥሃለሁ
በብዙ ምሥጋና ፊትህ እቀርባለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሌላ ቃላት የለኝም አንተን የማከብርበት
ግን አንዲያው ተመስገን ልበልህ በሰጠኸኝ አንደበት (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ኧረ እኔስ ምህረትህ እጅግ በዝቶልኛል
ብዙ ኃጢአቴን ይቅር ብለኸኛል
በዘመኔ ሁሉ ለአንተ እገዛለሁ
በገናዬን ይዤ ፊትህ እዘምራለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሌላ ቃላት የለኝም አንተን የማከብርበት
ግን አንዲያው ተመስገን ልበልህ በሰጠኸኝ አንደበት (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እኔም እንዳከብርህ አንተ መርጠኸኛል
በሞገስ ላይ ሞገስ ደርበህልኛል
ሁልጊዜ በደስታ አዜምልሃለሁ
ራሴን ዝቅ በማድረግ አንተን አክብራለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሌላ ቃላት የለኝም አንተን የማከብርበት
ግን አንዲያው ተመስገን ልበልህ በሰጠኸኝ አንደበት (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ