አንተ ገናና ነህ
Ante Genana Neh
2011 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ላሞግሰው ዙፋንህን ላደናንቅ
ከእግሮችህ ስር ሆኜ ቅኔን ላፈልቅ
አንደበቴን ቀድሼ ዜማ ላፈስ
ጌታ ልልህ መጣሁ ክበር ንገሥ
እንዲህ ከሚሉ ጋራ ልተባበር
እኔም የእራሴን ፈንታ ልጨምርልህ
ይሄም ትንሽ ነው ለአንተ አይበዛምና
ከናፍርቶቼ ይጥሩህ ብለው ገናና አንተ ገናና
አዝማች · Chorus
አንተ ገናና ነህ አንተ ገናና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በላይ ነህ ከዚህም በላይ ነህ
በላይ ነህ ከዚያም በላይ ነህ (፪x)
ከሰማነው እና ካየነው
በላይ ነህ ከዚህም በላይ ነህ
ከዘመርነው ከሰበክነው
በላይ ነህ ከዚያም በላይ ነህ (፪x)
የለም (፫x) ሌላ ጌታ የለም
የለም(፫x) ሌላ ንጉሥ የለም
የለም (፫x) ሌላ አዳኝ የለም
የለም (፫x) ሌላ ገዢ የለም
ሌላ ጌታ የለም ፣ ሌላ ንጉሥ የለም
ሌላ አዳኝ የለም ፣ ሌላ ገዢ የለም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በእውነትና በመንፍስ ስትመለክ
ፍጥረት ሁሉ በፊትህ ሲል ዝቅ ዝቅ
ቋንቋው ሁሉ ስለአንተ ዝና ሲያወራ
ሲባል ከአማልክት ሁሉ ነህ የተፈራህ
እንዲህ ከሚሉ ጋራ ልተባበር
እኔም የእራሴን ፈንታ ልጨምርልህ
ይሄም ትንሽ ነው ለአንተ አይበዛምና
ገና ፍጥሮችህ ይጥሩህ ብለው ገናና አንተ ገናና
አዝማች · Chorus
አንተ ገናና ነህ አንተ ገናና (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
በላይ በሰማይ ላለው በዙፋኑ
ለሚገዙለት እልፍ ቅዱሳኑ
ለሚባርኩ ስሙን በዝማሬ
አምላክ ለሆነው ጥንትም ቢሆን ዛሬ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
እኔም አለኝ አምልኮ
እኔም አለኝ ምሥጋና
እኔም አለኝ ዕልልታ
በአመታት መካከል
ጸንቶ ለሚኖረው
ለጌቶቹ ጌታ (፪x)
ለጌቶቹ ጌታ
ለነገሥታት ንጉሥ
ለጌቶቹ ጌታ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ