እንሂድ ሲሉኝ
Enehid Silugn
2011 · ትራክ 12 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንሂድ ሲሉኝ ወደ እግዚአብሔር ቤት
ደስ ካለኝ ሓሴት ካደረኩት
ስሄድማ ስገባ በፊቱ ሲቀበለኝ በብዙ ምህረቱ
ይጨምራል ይበዛል ደስታዬ በመንፈሱ ሲነካኝ ጌታዬ
በረከቱን ባዘዘበት ስፍራ ከዚያ ልሆን ከቅዱሳን ጋራ
ደግነቱን ባዘዘበት ስፍራ ከዚያ ልሆን ከወገኖች ጋራ
አዝማች · Chorus
አምላኬ ሆይ በቤትህ ሰላም አለ
ያዘነውን የሚያጽናና እያባበለ (፪x)
በዓለም ካለው የተለየ ሰላም ደስታ
አግኝቻለሁ ወደ ቤትህ እኔ ስመጣ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ወደ ቤትህ ልገስግስ በመንፈስህ እንድዳሰስ
ወደ ፊትህ ልገስግስ በእጆችህ እንድዳሰስ
ወደ ክብርህ ልገስግስ በውበትህ እንዲለኝ ደስ
ወደ ፀጋህ ልገግስ በመንፈስ እንዲለኝ ደስ
ሁል ጊዜ በፊትህ የሚቆሙ
ጥበብህን ከአንደበትህ የሚሰሙ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ባሪያዎችህ ኧረ እንደምን የታደሉ
በማደሪያህ ደፋ ቀና ሁሌ የሚሉ
በቤትህ ደፋ ቀና ሁሉ ሚሉ
ወደ ቤትህ ልገስግስ በመንፈስህ እንድዳሰስ
ወደ ፊትህ ልገስግስ በእጆችህ እንድዳሰስ
ወደ ክብርህ ልገስግስ በውበትህ እንዲለኝ ደስ
ወደ ፀጋህ ልገግስ በመንፈስ እንዲለኝ ደስ
ቁጥር 4 · Verse 4
ልዑል መጠጊያ ጥላ
ለዚህ ዓለም ሐሩር ከለላ
መኖሪያ ነህ በኧረፍት
አምላኬ ሆይ የአንተ ቢት
ሰው ሁሉ ይኖራል ታምኖ
ሳይሰጋ ምን ይሆናል ብሎ
በቤትህ በመቅደስህ ምትሸከም አንተ ነህ
አዝማች · Chorus
እንሂድ ሲሉኝ ወደ እግዚአብሔር ቤት
ደስ ካለኝ ሓሴት ካደረኩት
ስሄድማ ስገባ በፊቱ ሲቀበለኝ በብዙ ምህረቱ
ይጨምራል ይበዛል ደስታዬ በመንፈሱ ሲነካኝ ጌታዬ
በረከቱን ባዘዘበት ስፍራ ከዚያ ልሆን ከቅዱሳን ጋራ
ደግነቱን ባዘዘበት ስፍራ ከዚያ ልሆን ከወገኖች ጋራ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ