ክቡር
Kebur
2011 · ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከቶ አልደከመም ጉልበቱ
ከቶም አልደነዘም ስለቱ
ዛሬም አልፈዘዘም ውበቱ
ይገርማል የቃልህ ጽናቱ
አሁንም ይሰራል ያው ነው
በፍጥረት ሁሉ ላይ ገዢ ነው
ሰማያት ቢያልፉም ምድር
ቃልህ ለዘለዓለም ክቡር
አዝማች · Chorus
ክቡር (፫x) ቃሉ የእግዚአብሔር
ክቡር (፫x) ድምጹ የእግዚአብሔር
ክቡር (፫x) የእርሱ ንግግር
ቁጥር 2 · Verse 2
ድምጹ ተራራውን ያቀልጣል
ጠንካራውን ዝግባ ይቆርጣል
ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ ይገልጣል
ጌታዬ ሆይ ድምጽህ ያስፈራል
ቃልህ ሰማያትን አጽንቷል
ምድርን ደግሞ መስርቷል
ሕያውን ግዑዙንም ሰርቷል
በዘለዓለም ክብሩ ይኖራል
አዝማች · Chorus
ክቡር (፫x) ቃሉ የእግዚአብሔር
ክቡር (፫x) ድምጹ የእግዚአብሔር
ክቡር (፫x) የእርሱ ንግግር
ቁጥር 3 · Verse 3
ወጀብ ነው ወይ አውሎ ንፋሱ
ሰምቶ መልስ ያልሰጠው ለድምጹ
ግዑዝ ነው ወይ ሕያው ፍጥረት
ሰምተው ማይታዘዙት
በሰማያት ያሉ በምድር
ይገዛሉ ለእግዚአብሔር
በሁሉ ላይ ብርቱ ገናና
የእኔ ጌታ ብቻ ነውና
ከቶ አልደከመም ጉልበቱ
ከቶም አልደነዘም ስለቱ
ዛሬም አልፈዘዘም ውበቱ
ይገርማል የቃልህ ጽናቱ
አሁንም ይሰራል ያው ነው
በፍጥረት ሁሉ ላይ ገዢ ነው
ሰማያት ቢያልፉም ምድርም
ቃልህ ለዘለዓለም ክቡር
አዝማች · Chorus
ክቡር (፫x) ቃሉ የእግዚአብሔር
ክቡር (፫x) ድምጹ የእግዚአብሔር
ክቡር (፫x) የእርሱ ንግግር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ