እንታረቅ
Enetareq
2011 · ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አፍቅሮኝ ፍቅርን አስተማረኝ
የማረኝ ምህረት አድርጊ ያለኝ
በጌታ ለካ ይህም ይቻላል
ለአሳዳጅ ምህረት ይደረጋል
ገዳዬን በእጅህ ላይ አግኝቶ
መመለስ መንገድ አሳይቶ
እንዲህ ነው ለካ ፍቅር ማለት
ሁሉንም መቀበል በምህረት (፪x)
አዝማች · Chorus
ምህረት አግኝቼ ምህረት አሰጣለሁ
ይቅር ተብዪ ይቅር እላለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ህግ??? ሳናደርግ በመሃከላችን
መስዋዕት ለማቅረብ ምነው ችኮላችን
ይቅር መባባሉ ማንንስ ገደለ
ተቆጥተን መሸ ዋል አደርም አለ
እንታረቅ አሃሃሃ እንታረቅ
እንታረቅ አሆሆሆ እንታረቅ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አሁን እንታረቅ እርስ በእርሳችን
ሳንሰዋ በፊት መስ ዋዕታችንን
በአምላካችን ፊት እስቲ እንተቃቀፍ
የሰጠውንም ቃል ከቶ አንተላለፍ
እንታረቅ አሃሃሃ እንታረቅ
እንታረቅ አሆሆሆ እንታረቅ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምህረት አግኝቼ ምህረት አሰጣለሁ
ይቅር ተብዪ ይቅር እላለሁ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ታናሹን ከታላቁ እኩል
በአንድነት ማቀፍ መጠየቅ
በዳዩን መጠየቅ ይቅርታ
ይሄ ነው ወንጌሉ የጌታ
ለአፍቃሪ ፍቅር መስጠትማ
ያለ ነው በዓለም ከተማ
ጨካኝ ነው የሚሉትን ክፉ
ይቻላል በወንጌል/በጌታ ማቀፉ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምህረት አግኝቼ ምህረት አሰጣለሁ
ይቅር ተብዪ ይቅር እላለሁ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
እንታረቅ አሃሃሃ እንታረቅ
እንታረቅ አሆሆሆ እንታረቅ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ