ቅዱስ ነህ ቅዱስ
Qedus Neh Qedus
2011 · 4:55 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ቃላቶች ሁሉ አነሱብኝ ላመሰግንህ ፈልጌ
በማንስ ቋንቋ ላሞግስህ የእኔ ጌታ እንዴት አድርጌ
አምላኬ ሆይ አምላክ ነህ
ንጉሤ ሆይ ንጉሥ ነህ
ከዚህስ??? ሌላ ምን ለበልህ
ከዚህስ??? ሌላ ማን ልበልህ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ኧረ አንተ ታላቅ ነህ እጅግ ገናና
ቃል የማይገልጸው ውበትህ ዝናህ
የምድር ቋንቋ የሰው ቃላት
ለእኔ አነሰብኝ ላዜምበት
በመላዕክቱ ቋንቋ ልሳን
ቅዱስ ቅዱስ ነህ ቅዱስ ለበልህ (፪x)
እስቲ ልጥራው ስምህን ፍፁም ቅዱስ የሆነውን
አንተ በራስህ ቅዱስ በማንነትህ ቅዱስ
በስራህ ሁሉ ቅዱስ በአደራረግህ ቅዱስ
አንተ ብቻህን ቅዱስ በማንነትህ ቅዱስ
በስራህ ሁሉ ቅዱስ በአደራረግህ ቅዱስ
ቅዱስ ነህ ቅዱስ (ቅዱስ ነህ ቅዱስ)
ቅዱስ ቅዱስ (ቅዱስ ኢየሱስ) (፪x)
አዝማች · Chorus
ቃላቶች ሁሉ አነሱብኝ ላመሰግንህ ፈልጌ
በማንስ ቋንቋ ላሞግስህ የእኔ ጌታ እንዴት አድርጌ
አምላኬ ሆይ አምላክ ነህ
ንጉሤ ሆይ ንጉሥ ነህ
ከዚህስ ሌላ ምን ለበልህ
ከዚህስ ሌላ ማን ልበልህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የዙፋንህን ክብር ድምቀት
የግዛትህን ወሰን ስፋት
የጌትነትህን ስልጣን ብቃት
የስምህን ዝና አለቅነት
በተመረጠው ቃልና ቅኔ
ብዘምር/ብቀኘው እንኳን አልረካም እኔ (፪x)
እስቲ ልጥራው ስምህን ፍፁም ቅዱስ የሆነውን
አንተ በራስህ ቅዱስ በማንነትህ ቅዱስ
በስራህ ሁሉ ቅዱስ በአደራረግህ ቅዱስ
አንተ ብቻህን ቅዱስ በማንነትህ ቅዱስ
በስራህ ሁሉ ቅዱስ በአደራረግህ ቅዱስ
ቅዱስ ነህ ቅዱስ (ቅዱስ ነህ ቅዱስ)
ቅዱስ ቅዱስ (ቅዱስ ኢየሱስ) (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ