የተፈታው እስራቴ
Yetefetaw Eseratie
2011 · 5:26 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የታሰረችው ውርንጭላ ለኢየሱስ መቀመጫ
ታስፈልገዋለችና አምጧት በፍጥነት/በቶሎ ፍቱና (፪x)
ለምን ቢባል ሊከብርባት ፣ ለምን ቢባል ሊነግስባት
እራሱን በላዯ አድርጐ ኢየሩሳሌም ሊገባባት/ሊጓዝባት (፪x)
አዝማች · Chorus
የተፈታው እስራቴ የታወጀው አርነቴ
በቀራንዮ በጐልጐታ እራሱን ሲሰጥ ለእኔ ጌታ
ተፈጸመ ሲል ሲናገር የተጫነኝ ክፉ ቀንበር
ሲወድቅ አየሁ ሲሰባበር ይሁን ለእርሱ ብዙ ክብር
ቁጥር 2 · Verse 2
በድቅድቁ ጨለማ ተጥዬ ስደናበር
በጠበቀው ሰንሰለት ባማይፈታው እስር
እንድጠፋ ለሲዖል የታጨሁ በመሆኔ
በግፍ ነፍሴ ሊሰዋ ሊታረድ በጭካኔ
አዋጅ ወጣ ከሰማይ ከዙፋን ከመቅደሱ
ፍቷትና ትለቀቅ ተባለ ክብር ለእርሱ
አገኛታለሁ ብሎ የጐመጀው ጠላቴ
እፍረት ተከናነበ እኔም ጸና ጉልበቴ
አዝማች · Chorus
የተፈታው እስራቴ የታወጀው አርነቴ
በቀራንዮ በጐልጐታ እራሱን ሲሰጥ ለእኔ ጌታ
ተፈጸመ ሲል ሲናገር የተጫነኝ ክፉ ቀንበር
ሲወድቅ አየሁ ሲሰባበር ይሁን ለእርሱ ብዙ ክብር
ቁጥር 3 · Verse 3
አጥምዶብኝ ወጥመዱን እግሮቼ ስር ዘርግቶ
መረብ ውስጥ እንድገባ ፈልጐ እጅግ ጓጉቶ
መስሎት የተሳካለት የገባሁ በመዳፉ
ደስ ብሎት ጨፈረ ሊውጠኝ ይዞ በአፉ
የይሁዳው አንበሳ የቀራንዮ ጀግና
ጉልበተኛው ኢየሱስ ስመጥሩ ገናና
ፍፁም አይሆንም ብሎ ከሰማያት ወረደ
እራሱን ስለእኔ ሲሰጥ ጠላቴ ተዋረደ
አዝማች · Chorus
የተፈታው እስራቴ የታወጀው አርነቴ
በቀራንዮ በጐልጐታ እራሱን ሲሰጥ ለእኔ ጌታ
ተፈጸመ ሲል ሲናገር የተጫነኝ ክፉ ቀንበር
ሲወድቅ አየሁ ሲሰባበር ይሁን ለእርሱ ብዙ ክብር
ቁጥር 4 · Verse 4
ወገኖች የምስራች ተሸንፏል ዲያቢሎስ
የሞትን ጣር ባጠፋው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ
ከመስቀሉ ስር ያኔ አድቅቆታል ቀጥቅጦ
ለሚያምኑበት በሙሉ አስገዝቶታል ረግጦ
ወጥመዱ ተሰበረ ነፍሴ እንደወፍ በረረች
ሰይጣን ባዶ እጁን ቀረ ከግዞቱ አመለጠች
ሞትስ መውጊያው የታለ ጌታ ሞቶ ተነሳ
ከሲዖል ምርኮን ማርኮ በስልጣኑ ድል ነሳ
አዝማች · Chorus
የተፈታው እስራቴ የታወጀው አርነቴ
በቀራንዮ በጐልጐታ እራሱን ሲሰጥ ለእኔ ጌታ
ተፈጸመ ሲል ሲናገር የተጫነኝ ክፉ ቀንበር
ሲወድቅ አየሁ ሲሰባበር ይሁን ለእርሱ ብዙ ክብር (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ