Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በየቀኑ በየዕለቱ

Beyeqenu Beyeletu

2011 · ትራክ 7 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በየቀኑ በየእለቱ በየማለዳው የማየው

የጌታዬን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነው

በየእለቱ በየቀኑ በየማለዳው የማየዉ

የኢየሱሴን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነው

የወደዳቸውን ፈጽሞ እስከመጨረሻው ወደደ

ልጆቹን ከበደል ሊያነፃ በእራሱ ላይ ሞትን ፈረደ

ከሞት ይልቅ እጅግ ያየለ የበረታ ፍቅር ይዞት

ኢየሱስ እራሱን ከፈለ የእኔ መጥፋት አሳዝኖት

እነሆ ሲነጋና ሲመሽ ይህን/የእርሱን ፍቅር አስታውሰዋለሁ

ሌለ ምሰጠው የለምና ተመስገን ከፍ በል እለዋለሁ (፪x)

በየቀኑ በየእለቱ በየማለዳው የማየው

የጌታዬን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነው

በየእለቱ በየቀኑ በየማለዳው የማየዉ

የኢየሱሴን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነው

ፍቅር ምን እንደሆነ ታወቀ በስራው በኃይሉ በርትቶ

ሰማይን ከምድር አስታረቀ በምህረቱ ጉልበት ጐትቶ

የጥሉ ግድግዳ ፈረሰ ሆነ እርቅ ሰላም ደስታ

የራቀው በሙሉ ቀረበ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን በጌታ

አቤት ይሄ ጌታ ቸርነቱ አደራረጉ አስገርሞኛል

በእውቀት በችሎታና ጥበቡ ወደ ፍቅሩ ግዛት አድርሶኛል (፪x)

እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ኧረ ለምን ለምን

ግን ይህንን ብቻ አውቃለሁ እኔ መወደዴን

ይህንን ብቻ አውቃለሁ የወደደኝን

በጉያው በእቅፉ አስገብቶ እንደሰወረኝ

አውቃለሁ ኢየሱስ ሁልጊዜ እንደሚያስብልኝ (፪x)

በየቀኑ በየእለቱ በየማለዳው የማየው

የጌታዬን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነው

በየእለቱ በየቀኑ በየማለዳው የማየዉ

የኢየሱሴን ብዙ ምህረት ብዙ ፍቅሩን ብቻ ነው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ