አጠገቤ ነህ
Ategebe Neh
2008 · 6:38 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አልበር እንደ ንስር ከደመናው በላይ
ወዴት ነው መገኛህ ስፍራ ወሰን አለው ወይ
በወርድ ቆላ ብወጣ ወደ ደጋ
ውስጥ ውስጤን ታወቀኝ ጌታ አለ ከኔጋ
አጠገቤ ነህ ጌታ አጠገቤ
ዘልቀህ ገብተሃል ከውስጥ ከልቤ
ይታወቀኛል ሁሌ አብሮነትህ
ሰላም ተሰማኝ በመገኘትህ
አዝማች · Chorus
ሁሉ ሰላም ነው ጌታ ካለ
ሁሉ ደህና ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ሁሉ በጎ ነው ጌታ ካለ
ሁሉ ሸጋ ነው
ውስጤን ስሰማው ሳደምጠው
ሁሉ ሰላም ሰላም ነው
ውጪውን አይቶ ልቤ እንዳሰጋ
እርፍ አለ ባንተ ተረጋጋ
ቁጥር 3 · Verse 3
እሩቅ አይደለህም ካለሁበት አለህ
እስከ ምድር ጫፍ ብሄድ በዛም ትገኛለህ
ፍጥረት ባንተ አብሮ የለህም ብትባል
ምስክር አልሻም ስራህ ይናገራል
አጠገቤ ነህ ጌታ አጠገቤ
ዘልቀህ ገብተሃል ከውስጥ ከልቤ
ይታወቀኛል ሁሌ አብሮነትህ
ሰላም ተሰማኝ በመገኘትህ
አዝማች · Chorus
ሁሉ ሰላም ነው ጌታ ካለ
ሁሉ ደህና ነው
ቁጥር 4 · Verse 4
ሁሉ ሰላም ነው ጌታ ካለ
ሁሉ ደህና ነው
ውስጤን ስሰማ ሳደምጠው
ሁሉ ሰላም ሰላም ነው
ውጪውን አይቶ ልቤ እንዳሰጋ
እርፍ አለ ባንተ ተረጋጋ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ