Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሰማይን የሰራ

Semayen Yesera

2008 · 5:05 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከሰማያት በላይ ያለኸው

እረድኤታችን የሆንከው

ከደመናት በላይ ተራምደሃል

እግዚአብሔር ማንስ ይመስልሃል (፪x)

ማነው ሰማይን የሰራ

ማነው ምድርን ያፀና

ሌላው ካንተ በቀር የለም

ጌታ ነህ ክበር ለዘላለም (፪x)

ጌታ ክበር ለዘላለም

ጌታ ንገስ ለዘላለም

ይነሳና እስኪ ይናገር

አምላክ ማነው ከአንተስ በቀር

በጉልበትህ ጽናት ተራምደህ

ትኖራለህ ሁልጊዜ ከብረህ (፪x)

ታላቅነትህ ቢወራ ቢነገር

ምንም አይገልጽህ ከመደነቅ በቀር (፪x)

እንዲያው ዝም ብዬ ባለኝ አቅም

ብዬ ልለፈው እንዳተ የለም (፪x)

(እስኪ ማነው)

ማነው ሰማይን የሰራ (የሰራ)

ማነው ምድርን ያቀና (ያጸና)

ሌላው ካንተ በቀር የለም (የለም የለም)

ጌታ ነህ ግዛን ለዘላለም (ለዘላለም) (፪x)

ጌታ ክበር ለዘላለም

ጌታ ንገስ ለዘላለም (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ