ማን ያንከባለው
Man Yankebalew
2008 · 5:31 · አማርኛ
ማን ያንከባለው ይህን ድንጋይ
ብዬ ስማትር ታች ላይ
ቀና ብዬ እንዳይ አደረከኝ
ለካስ ተንከባሏል ያስጨነቀኝ (፪x)
አሻቅቦ ማየት ከሁኔታ በላይ
አድርጎኛል ጌታ ችግርን እንዳላይ
ሻገር ሻገር ብሎ አይኔ ከሩቅ አይቶ
ያመሰግንሃል ሁሉን በአንተ ረስቶ (፪x)
ይኸው (፬x)
ጌታ ተቀበለው ምሥጋናዬ ይኸው
ጌታ ተቀበለው አምልኮዬ ይኸው (፪x)
ጭንቅ ጥብብ ወየው ያልኩበት
አንገት ያስደፋኝ ያለቀስኩበት
ያኔ ያስፈራራኝ ልቤን ያራደው
ተንከባለለ ከፊቴ ያለው (፪x)
አሻቅቦ ማየት ከሁኔታ በላይ
አድርጎኛል ጌታ ችግርን እንዳላይ
ሻገር ሻገር ብሎ ዓይኔ ከሩቅ አይቶ
ያመሰግንሃል ሁሉን በአንተ ረስቶ (፪x)
ይኸው (፬x)
ጌታ ተቀበለው ምሥጋናዬ ይኸው
ጌታ ተቀበለው አምልኮዬ ይኸው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ