ጎዳና ላይ
Godana Lay
2008 · 5:50 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምልክት አለብኝ አንተ እንደረዳኸኝ
ተጥሎ የኖረ ያቁስለኛ እኔ ነኝ
ምልክት አለብኝ በሰውነቴ ላይ
ሁሉን የረሳሁት ጌታ ባንተ አይደል ወይ/2
አዝማች · Chorus
ባንተ ነው ነው ጌታ ባንተ ነው
ቁስለኛው ተነስቶ ሰው የሆነው
ባንተ እኮ ነው ነው ጌታ ባንተ ነው
ምስኪኑ ተነስቶ ሰው የሆነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ጎዳና ላይ ጎዳና ላይ
እንዳላየ ሆኖ ስንቱ አልፎኝ የለ ወይ
ለየት ይላል ዛሬስ የገጠመኝ
ሰው ቢርቅ እኔ አለው አለኝ
ይሄማ ይወራ ይህማ ይነገር
አንተ ባትደርስልኝ ምን ይወጠኝ ነብር/2
ይሄማ ይወራ ይህማ ይነገር
ጌታ ባትደርስልኝ ምን ይወጠኝ ነብር/2
አዝማች · Chorus
ኧረ እንዴት እሆን ነበር ያገዘኝ ጌታዬ ይክበር
እኮ እንዴት እሆን ነበር የረዳኝ ጌታዬ ይክበር
እስቲ እንዴት እሆን ነበር ያገዘኝ ጌታዬ ይክበር
ቁጥር 3 · Verse 3
ያልጠገረ ተስፋው ተሟጦ
በቤተ መቅደስ ደጅ ተቀምጦ
ከሚወጣና ከሚገባው ሰው
እየለመነ ፊት የገረፈው እኔው ነኝ ያ ሰው
ድንገት ተነስቶ ከመቅደስ ገባ
የሚያየው ሁሉ ግራ እስኪጋባ
አመሰገነ ባደባባይ ምን ነካው የሚል ማነውስ ከልካይ/2
ተመስገን ይላል ከፍ በል ይላል
እርሱም እንደሰው ወግ ማረግ አይቷል/2
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ