በል ደህና ውጣ
Bel Dehna Wita
2008 · 4:31 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በል ደህና ውጣ በል ደህና ግባ
ተብያለሁኝ ልቤ እንዳይሰጋ/2
ምንም አይቆምም ከፊት ለፊቴ
ተረክቦኛል እጁ ላይ ነው ቤቴ/9
ኮራ በል እንጂ ዛሬም ኮራ በል
ቀና ብለህ ሂድ ደፋ ደፋ አትበል
ኑር ሰላም ብሎ ዘላለሜን ያዘው
ክብር ይሁንለት ልቤን ላሳረፈው
አዝማች · Chorus
ቅጥር ቀጠረልኝ ጠላቴ ማይደፍረው/2
ታዲያ ምን አሰጋኝ ዚሪያዬን ቢዞረው
የምታመንበት ጌታ ከኔ ጋር ነው
ከኔ ጋር ነው ጌታ ከኔ ጋር ነው
ይረፍ እንዲ ልቤን ምን አሰጋው
ከኔ ጋር ነው ጌታ ከኔ ጋር ነው
ይረፍ እንዲ ልቤን ምን አሰጋው
ቁጥር 2 · Verse 2
አይዞህ ብሎኛል ሁሉን ቻዩ አባቴ
ተደላደልኩኝ ፀናልኝ ጉልበቴ
ያለማቋረጥ ጠላቴ ቢዞረኝ
ጌታዬን ይዤ ኧረ ምን አሰጋኝ
ቅጥር ቀጠረልኝ ጠላቴ ማይደፍረው/2
ታዲያ ምን አሰጋኝ ዚሪያዬን ቢዞረው
አዝማች · Chorus
የምታመንበት ጌታ ከኔ ጋር ነው
ከኔ ጋር ነው ጌታ ከኔ ጋር ነው
ይረፍ እንዲ ልቤን ምን አሰጋው
ከኔ ጋር ነው ጌታ ከኔ ጋር ነው
ይረፍ እንዲ ልቤን ምን አሰጋው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ