Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አይጥልም

Aytelem

2008 · ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አይጥልም አይረሳም አይጥልም አይረሳም (፪x)

ሰው ማድረግ ይችላል አይጥልም አይረሳም

ከአመድ ላይ ያነሳል አይጥልም አይረሳም (፪x)

አቅም ጉልበት አጣሁ ብሎ በፍራቻ ለሚያለቅሰው

ሰው የሌለው የተረሳ እምባው ምግቡ የሆነ ሰው

ተስፋው ድሉ ጨልሞበት የሞቱን ቀን ለጠበቀው

ዛሬ በቃ የለቅሶ ቀን እግዚአብሔር ሲጐበኘው (፪x)

አይጥልም አይረሳም አይጥልም አይረሳም (፪x)

ሰው ማድረግ ይችላል አይጥልም አይረሳም

ከአመድ ላይ ያነሳል አይጥልም አይረሳም (፪x)

በመንፈቀ ሌሊት ቀሰቀሰኝ ዘምር ብሎ አዶናይ

ኢየሱስ ነው ይክበር በዝማሬ

በዓለም ላይ የሌለ ሚስጥረኛ ታማኝ ትጉ ደግ እረኛ

ኢየሱስ ነዉ የልቤ እረኛ (፪x)

ቀን ሲከፋ ስጨላልም አይዞህ የሚል ወዳጅ የለም

በደህና ቀን የነበረው በክፉ ቀን ምን ወሰደዉ

የእኔስ አባት ለየት ይላል በመከራ ቀን ይደርሳል

እርሱን ታምኖ ለሚጣራ ከተፍ ይላል የሚያኮራ (፪x)

እኔን ያከበሩ ይከብራሉ የናቁኝም ይናቃሉ

ብሏልና አባቴ በቃሉ

እሱን ላከበረው ለታመነው በመንገዱ ለሚጓዘው

ከቶ አየውድቅም ጠንካራ ግንብ አለው

አይጥልም አይረሳም አይጥልም አይረሳም (፪x)

ሰው ማድረግ ይችላል አይጥልም አይረሳም

ከአመድ ላይ ያነሳል አይጥልም አይረሳም (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ