ነገር አለኝ
Neger Alegn
2008 · ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔስ ቃሉን ስገልጠው የገረመኝ
የእምነት አባት ስላለኝ ስላለኝ
እኔስ ቃሉን ስገልጠው መንፈስ ነካኝ
የእምነት አባት ስላለኝ ስላለኝ
ብቻውን ቆሞ በአደባባይ
ትወራረደ ጌታን ሊታይ
በእሳት ተገልጦ አስደንቆታል
የኤልያስ አምላክ እኔስ ገርሞኛል
ቢወዳደሩ ከእግዚአብሔር ጋራ
ፊት ብቧጥጡ በዓል ቢጠራ
ሳይመጣ ቀርቶ ጉድ አረጋቸው
አንድም ሳይቀሩ አስጨረሳቸው
አዝማች · Chorus
ነገር አለኝ እኔስ ነገር አሃሃ (፪x)
አለና ሚወጋ በጠላት ሰፈር
ጩኸት አለኝ እኔስ ነገር አሃሃ (፪x)
በሰባተኛው ቀን ይፈርሳል ቅጥር
ይታመናል እግዚአብሔር ይታመናል (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አዋጅ ቢታወጅ አዋጁን ሽሬ
አመልከዋለሁ ጌታ ነው ክብሬ
የዳንኤል አምላክ የማመልከዉ
አዋጅ ገልብጦ ሚያዘምር ነዉ (፪x)
አኔማ አዋጅ ቢታወጅ እኔማ አዋጁን ሽሬ
እኔማ አመልከዋለሁ እኔ ጌታ ነው ክብሬ (፪x)
አዝማች · Chorus
ነገር አለኝ እኔስ ነገር አሃሃ (፪x)
አለና ሚወጋ በጠላት ሰፈር
ጩኸት አለኝ እኔስ ነገር አሃሃ (፪x)
በሰባተኛው ቀን ይፈርሳል ቅጥር
ይታመናል እግዚአብሔር ይታመናል (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መነሻም የለኝ ከተደፋሁ
በዙፋኑ ሥር አመሻለሁ
ፊቱ ወድቄ ተባረክ ስለዉ
ይለቅልኛል መንፈሱን ሰማይ ክፍት ነዉ (፪x)
እኔማ ማምለክ ጀምሬ እኔማ መቼ አቆማለሁ
እኔማ የነካኝ ክብር እኔ ለየት ያለ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ነገር አለኝ እኔስ ነገር አሃሃ (፪x)
አለና ሚወጋ በጠላት ሰፈር
ጩኸት አለኝ እኔስ ነገር አሃሃ (፪x)
በሰባተኛው ቀን ይፈርሳል ቅጥር
ይታመናል እግዚአብሔር ይታመናል (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ