የአምላኬ
Yeamlakie
2008 · ትራክ 11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ያምላኬ ጉዳይ ከበደብኝ
ቅጥሩ ፈርሶ ስላየሁኝ
ልቤን ላስታመው ደግሞ ምግብ አልበላ
ቅጥሩ ታድሶ ካላየሁማ
ኧኸ ጦቢያው ሰምበላት
ኧኸ ውረድ ሲሉኝ
አዝማች · Chorus
ቅጥር ልሰራ ሄጃለሁኝ (፪x)
ና ውረድ ሲሉኝ (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ስፍራው ተመችቶኝ እዛው ቀረሁኝ
አልወርድም አልወርድም ከተራራው ላይ
የእግዚአብሔርን ክብር በዓይኖቼ እስከማይ
አልዛቤል ምድሩን ሃገሩን ገዝታ
ምን ሰላም አለ ለእኛ መኝታ
እረፍት የለኝም ለሽፋሽፍቴ
እስካያት ድረስ ወድቃ ከፊቴ
ኧኸ ውሻ ሲበላት
ኧኸ በዓይኔ አያለሁ
አዝማች · Chorus
የትናገረኝ ጌታ ታማኝ ነው (፪x)
ና ውረድ ሲሉኝ (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ስፍራው ተመችቶኝ እዛው ቀረሁኝ
አልወርድም አልወርድም ተራራው ላይ
የእግዚአብሔርን ክብር በዓይኖቼ እስከማይ
ቤቱ በሸቀጥ ነጋዴ ሞልቶ
አጠራው ጌታ ጅራፍን ሰርቶ
ሁሉም ይሰግዳል ለአብ ክብር
ቤቱ ሲጠራ የእግዚአብሔር
ኧኸ የቤቱ ቅናት
ኧኸ እኔን በልቶኛል
አዝማች · Chorus
ቤቱ ሲጠራ በዓይኔ ያሳየናል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ