አኔን ያየ
Enien Yaye
2008 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አታልፍም ብሎ መንገዴን ዘግቶ
ሲፎክርብኝ ጠላቴ ቆሞ
ድንገት እግዚአብሔር ክንዱን ዘረጋ
የጠላቶቼ ወገብ ተወጋ
አታልፍም ብሎ መንገድ ቢዘጋ
በግራ በቀኝ እኔን ቢዋጋ
እጄን ይዞ መራኝ ሌሊቱ ነጋ
አታልፍም ብሎ መንገዴን ዘግቶ
ሲፎክርብኝ ጠላቴ ቆሞ
ድንገት እግዚአብሔር ክንዱን ዘረጋ
የጠላቶቼ ወገብ ተወጋ
አዝማች · Chorus
እኔን ያየ ጠላቴ ድብን ይበል ጠላቴ
እኔን ያየ ጠላቴ እርር ይበል ጠላቴ (፪x)
ድብን ይበል ጠላቴ እርር ይበል ጠላቴ
ቅጥል ይበል ጠላቴ እርር ይበል ጠላቴ
እስቲ እንበል እልልታ (፪x)
ሞትን ድል ላደረገው ጌታ ይገባዋል እልልታ
እስቲ እንበል ሽብሸባ (፪x)
ሞትን ድል ላደረገው ጌታ ይገባዋል ሽብሸባ
ቁጥር 2 · Verse 2
ይሞታል ብሎ ጠላት ሲያወራ
አይወርስም ብሎ ጠላት ሲያወራ (፪x)
አሻገረኝ ጌታ የበላይ ነውና (፬x)
አልቆ ነበረ የኔ ጉዳይ
ጌታ ባይመጣ ወርዶ ከላይ (፪x)
አትሞትም ብሎ ሞቴን ሰበረው
የሞትን መውጊያ ድል አደረገው
ድል አደረገው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አታልፍም ብሎ መንገዴን ዘግቶ
ሲፎክርብኝ ጠላቴ ቆሞ (፪x)
ድንገት እግዚአብሔር ክንዱን ዘረጋ
የጠላቶቼ ወገብ ተወግቶ
ወገብ ተወጋ (፪x)
አታልፍም ብሎ መንገድ ቢዘጋ
በግራ በቀኝ እኔን ቢዋጋ
እጄን ይዞ መራኝ ሌሊቱ ነጋ
አታልፍም ብሎ መንገዴን ዘግቶ
ሲፎክርብኝ ጠላቴ ቆሞ
ድንገት እግዚአብሔር ክንዱን ዘረጋ
የጠላቶቼ ወገብ ተወጋ
አዝማች · Chorus
እኔን ያየ ጠላቴ ድብን ይበል ጠላቴ
እኔን ያየ ጠላቴ እርር ይበል ጠላቴ (፪x)
ድብን ይበል ጠላቴ እርር ይበል ጠላቴ
ቅጥል ይበል ጠላቴ እርር ይበል ጠላቴ
እስቲ እንበል እልልታ (፪x)
ሞትን ድል ላደረገው ጌታ ይገባዋል እልልታ
እስቲ እንበል ሽብሸባ (፪x)
ሞትን ድል ላደረገው ጌታ ይገባዋል ሽብሸባ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ