Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ዘንድሮማ

Zenderoma

2008 · ትራክ 6 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከትላንቱ ዛሬ ሕይወቴ አምሮበታል

ለቅሶ ማታ ነበረ ጠዋት ደስታ ሆኗል

ውድቀቴን ድክመቴን ለሚፈልገው

ሄዳችሁ ንገሩት ዛሬም እንዳለሁ (፪x)

ዘንድሮማ ዘመን መጥቶልኛል (፪x)

አሁንማ ዘመን መጥቶልኛል (፪x)

ለእርሱ ሲመሽበት ለኔ ንጋት ሆኗል (፫x)

ያስለቀሰኝ ጠላት ዛሬ ግን አልቅሷል

ጨለማዬ በርቶ ሁሌ ያዘምረኛል (፪x)

ዘንድሮማ ዘመን መጥቶልኛል (፪x)

አሁንማ ዘመን መጥቶልኛል (፪x)

ህልምን አየሁ ብሎ ላባቱ ቢያወራ

ወንድሞቹ ቀንተው ሸጡት እንደባሪያ

ዘመን ሲመጣለት ዙፋን ላይ ሲወጣ

ሁሉም ሰገዱለት በተራ በተራ (፪x)

ለእርሱ ሲመሽበት ለኔ ንጋት ሆኗል (፫x)

ያስለቀሰኝ ጠላት ዛሬ ግን አልቅሷል

ጨለማዬ በርቶ ሁሌ ያዘምረኛል

ዘንድሮማ ዘመን መጥቶልኛል (፪x)

አሁንማ ዘመን መጥቶልኛል (፪x)

እንዲህ አልነበረም ባለፉት ዘመናት

የእኛ ቤት ሲፈተሽ የመከራው ብዛት

የፈረሰው ቅጥር በኢየሱስ ታድሶ

ዛሬም ይዘመራል ገደቡ ተጥሶ (፪x)

ዘንድሮማ ዘመን መጥቶልኛል (፪x)

አሁንማ ዘመን መጥቶልኛል (፪x)

ለእርሱ ሲመሽበት ለኔ ንጋት ሆኗል (፫x)

ያስለቀሰኝ ጠላት ዛሬ ግን አልቅሷል

ጨለማዬ በርቶ ሁሌ ያዘምረኛል

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ