ውለታው
Weletaw
2008 · ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኧረ እንዴት ነው ውለታው የእርሱ ፍቅር
እንዴት ብዬ ኧረ እኔስ እንዴት ልናገር (፪x)
እጅግ በዛ ውለታው ከአእምሮዬ በላይ ነው(፪x)
ኧረ እንዴት ነው ውለታው የእርሱ ፍቅር
እንዴት ብዬ ኧረ እኔስ እንዴት ልናገር (፪x)
እጅግ በዛ ውለታው ከአእምሮዬ በላይ ነው(፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እጅና እግሩን ጐኑን በጦር የተወጋው
እጅና እግሬ ሰውነቴ ጤነኛ እንዲሆን ነው
የሾህ አክሊል ደፍቶ በመስቀል የዋለው
እጅና እግሬ ሰውነቴ ጤነኛ እንዲሆን ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
እጅግ በዛ ውለታው ከአእምሮዬ በላይ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ተራራ ሸለቆ አቀበት ሲወጣ
የእኔን ስቃይ የኔን ውርደት ጌታ ወስዶልኝ ነው
በጅራፍ ሲገረፍ በጥፊ ሲመታ
የእኔን ስቃይ የኔን ውርደት ጌታ ወስዶልኝ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ኧረ እንዴት ነው ውለታው የእርሱ ፍቅር
እንዴት ብዬ ኧረ እኔስ እንዴት ልናገር (፪x)
እጅግ በዛ ውለታው ከአእምሮዬ በላይ ነው(፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መስቀል ተሸክሞ እንዲያ ሲንገላታ
ኢየሱሴ ለኔ ብሎ በደዌ ተመታ
የሕማም ሰው ሆነ በዝቶበት አበሳ
ኢየሱሴ ለእኔ ብሎ በደዌ ተመታ (፪x)
አዝማች · Chorus
እጅግ በዛ ውለታው ከአእምሮዬ በላይ ነው (፪x)
ኧረ እንዴት ነው ውለታው የእርሱ ፍቅር
እንዴት ብዬ ኧረ እኔስ እንዴት ልናገር (፪x)
እጅግ በዛ ውለታው ከአእምሮዬ በላይ ነው(፪x)
ኧረ እንዴት ነው ውለታው የእርሱ ፍቅር
እንዴት ብዬ ኧረ እኔስ እንዴት ልናገር (፪x)
እጅግ በዛ ውለታው ከአእምሮዬ በላይ ነው(፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ