ትወደኛለህ
Tewedegnaleh
2008 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንደምንም ብዬ እደርስበታለሁ
የተናገረኝን ህጄ እወርሳለሁ
ምን ሰልፉ ቢበዛ ውጊያው ቢጠነክር
ጸጋው ይረዳኛል አይቶልኛል ክብር
አዝማች · Chorus
ትወደኛለህ ይህን አውቃለሁ (፪x)
ከፍታ ነው ለኔ ያስቀመጥከው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ያ የተስፋ ቃሌ የእኔማ
ወሩ እንደደረሰ ተሰማ
ሰፈጸም በእምነት አይቼ
ልጠብቅ እጆቼን ዘርግቼ (፪x)
አዝማች · Chorus
ትወደኛለህ ይህን አውቃለሁ (፪x)
ከፍታ ነው ለኔ ያስቀመጥከው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ያመጐናጸፊያ ወደቀብኝና
ላገልግሎት ጠራኝ ጌታ ለየኝና
በቃ ላገልግለው ወገቤን ታጥቄ
መንፈሱን ልጠብቅ የሥጋዬን ንቄ
አዝማች · Chorus
ትወደኛለህ ይህን አውቃለሁ (፪x)
ከፍታ ነው ለኔ ያስቀመጥከው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ክብር አለ ብሎ ሲነግረኝ
ጌታዬን መለመን ጀመርኩኝ
ሰፈጸም በእምነት አይቼ
ልጠብቅ እጆቼን ዘርግቼ (፪x)
አዝማች · Chorus
ትወደኛለህ ይህን አውቃለሁ (፪x)
ከፍታ ነው ለኔ ያስቀመጥከው (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
የነገረን ትንቢት አካል ይለብስና
እኔም በተራዬ በሳቅ እሞላና
በጣር ክፍሌ ላይ እኔም እቆምና
ኢየሱስ ይከብራል በኔ እንደገና
አልችልም ብዬም አልልም
ስንፍናን በአፌ አላወራም
ቻይ ነው ጌታዬ ቻይ ነው
አይሆንም ብዬም አልልም
ስንፍናን በአፌ አላወራም
ቻይ ነው ጌታዬ ቻይ ነው
ያየተስፋ ቃሌ የኔማ
ወሩ እንደደረሰ ተሰማ
ሰፈጸም በእምነት አይቼ
ልጠብቅ እጆቼን ዘርግቼ (፪x)
ቻይ ነው ጌታዬ ቻይ ነው (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ