Azeb Hailu/Embi/Melas Hulu
2003 · ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አላደርግም ለሌላ ስግደት አንተ ብቻ ነህ አባት (፪x)
አልችልም ለሌላ መንበርከክ አንተ ብቻ ነህ አምላክ (፪x)
አላሰማም ለሌላ እልልታ ላንተ ብቻ ነው ይህ ጌታ (፪x)
እኔ አልሰዋም ለሌላ አምልኮ ለሥምህ ብቻ ነው እኮ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምላስ ሁሉ ያንተን ክብር ይናገረው ያውራ (፪x)
ጉልበት ሁሉ ተንበርክኮ ይደነቅ በስራህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ባሕር ከፍለህ ሕዝብህን ማሻገርህን
የልጆችህን ጠላት በዚያ ማስጠምህን
በምድረ በዳው ላይ መናን ማውረድህን
ከደረቀው አለት ውሃ ማፍለቅህን
(ኦሆ) ታምራትህ (ኦሆ) ድንቅህን ሁሉ
(ኦሆ) ይናገረው (ኦሆ) ምላስ ሁሉ
(ኦሆ) ታምራትህን (ኦሆ) ድንቅህን ሁሉ
(ኦሆ) ይዘምረው (ኦሆ) ምላስ ሁሉ
አዝማች · Chorus
ምላስ ሁሉ ያንተን ክብር ይናገረው ያውራ (፪x)
ጉልበት ሁሉ ተንበርክኮ ይደነቅ በስራህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ማይፈወሰውን ደዌ ማዳንህን
የሞተውን ከመቃብር ማንሳትህን
ሁለት ዓሣ ለአምስት ሺህ ማጥገብህን
በውሃም ላይ መሄድ መጓዝ መቻልህን
(ኦሆ) ታምራትህ (ኦሆ) ድንቅህን ሁሉ
(ኦሆ) ይናገረው (ኦሆ) ምላስ ሁሉ
(ኦሆ) ታምራትህን (ኦሆ) ድንቅህን ሁሉ
(ኦሆ) ይዘምረው (ኦሆ) ምላስ ሁሉ
አዝማች · Chorus
ምላስ ሁሉ ያንተን ክብር ይናገረው ያውራ (፪x)
ጉልበት ሁሉ ተንበርክኮ ይደነቅ በስራህ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ስለ ሰዎች ሃጥያት ራስህን መስጠትህን
በመስቀል ላይ ተቸንክረህ መሞትህን
ከሙታንም በኩር ሆነህ መውጣትህን
በአባትህ ቀኝ ኦ በክብር መሆንህን
(ኦሆ) ታምራትህ (ኦሆ) ድንቅህን ሁሉ
(ኦሆ) ይናገረው (ኦሆ) ምላስ ሁሉ
(ኦሆ) ታምራትህን (ኦሆ) ድንቅህን ሁሉ
(ኦሆ) ይመስክረው (ኦሆ) ምላስ ሁሉ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ