ለጌትነቱ
Legietenetu
2003 · ትራክ 7 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ለጌትነቱ ወሰን የለዉ
ይህንን አምላክ ማን ልበለዉ
በምንስ ቋንቋ ስለርሱ ላውራ
ታምራቶቹን የፍቅሩን ሥራ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
(አሃሃሃሃ) ከምድር ጫፍ እስከ ጫፍ
(አሃሃሃሃ) እርሱን ያመልካሉ
(አሃሃሃሃ) ትዕዛዙን ይሰማል
(አሃሃሃሃ) ንፋስ ማዕበሉ
የሰማይ ሠራዊት የሚያውጁለት
በጐነቱንና የርሱን ጌትነት (፪x)
አዝማች · Chorus
ለጌትነቱ ወሰን የለዉ
ይህንን አምላክ ማን ልበለዉ
በምንስ ቋንቋ ስለርሱ ላውራ
ታምራቶቹን የፍቅሩን ሥራ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
(አሃሃሃሃ) ክብርን እንዲያወሩ
(አሃሃሃሃ) ያበጃጀሃቸው
(አሃሃሃሃ) የሚያሞጋግሱህ
(አሃሃሃሃ) እንዴት ብዙ ናቸው
አእላፋት በሰማይ እልፎች በምድር
ድንቅ ነህ ይሉሃል አንተን እግዚአብሔር
አእላፋት በሰማይ እልፎች በምድር
ጌታ ነህ ይሉሃል አንተን እግዚአብሔር
አዝማች · Chorus
ለጌትነቱ ወሰን የለዉ
ይህንን አምላክ ማን ልበለዉ
በምንስ ቋንቋ ስለርሱ ላውራ
ታምራቶቹን የፍቅሩን ሥራ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
(አሃሃሃሃ) አፍ ያለው የሌለው
(አሃሃሃሃ) መልእክት አለኝ ይላል
(አሃሃሃሃ) የሰራኝ እግዚአብሔር
(አሃሃሃሃ) ነው ብሎ ያወራል
በግራና በቀኝ በሁሉም አቅጣጫ
ፍጥረት የሚያወራው ያንተን ችሎት ብቻ
በግራና በቀኝ በሁሉም አቅጣጫ
ፍጥረት የሚያወራው ያንተን ስልጣን ብቻ
አዝማች · Chorus
ለጌትነቱ ወሰን የለዉ
ይህንን አምላክ ማን ልበለዉ
በምንስ ቋንቋ ስለርሱ ላውራ
ታምራቶቹን የፍቅሩን ሥራ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ