የዳዊት
Yedawit
2003 · ትራክ 12 · 4:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የዳዊት የአብርሃም ልጅ ያሉት
ነብያት ቀድመው የተረኩት
በድንግል በማርያም ያደረ
የትውልድ ሐረግ ያስቆጠረ
ልደቱ በቤተልሔም
በንጉሥ በሄሮድስ ዘመን
እረኞች በግርግም ያዩት
ኢየሱስ የእኔ መድኃኒት
የይሁዳ ምድር አንቺ ቤተልሔም
ከይሁዳ ግዛቶች ከቶ አታንሺም
እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ካንቺ ይወጣል
ተብሎ እንደተነገረ ኢየሱስ ተወልዷል
አዝማች · Chorus
መልአኩ ወደ ማርያም ገብቶ
የሰላም ድምጹን አሰምቶ
አምላኬ ፀጋ የሞላብሽ
ማርያም ሆይ በይ ደስ ይበልሽ
እነሆ ልጅን ትወልጃለሽ
ሥሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ
በያዕቆብ ቤት ሁሉ ይነግሳል
የእግዚአብሔር ልጅ እርሱም ይባላል
ቁጥር 2 · Verse 2
ነፍሴ ጌታን ትባርከው መንፈሴም አምላኬን
ውርደቴን ተመልክቷል የባሪያይቱን
ብርቱ የሆነው እርሱ በእኔ ክብሩን ገልጧል
ትዕቢተኛን አዋርዶ ትሁቱን አክብሯል
ቃል ነበር ቃልም እግዚአብሔር
ይህም ቃል በአብ ዘንድ ነበር
በእርሱ ሕይወት ትኖራለች
ሕይወትም የሰው ብርሃን ነች
ቁጥር 3 · Verse 3
ከሆነው አንዳች አለእርሱ
አልሆነም ሁሉ ሆነ በርሱ
ዓለምን ያጸናበት ቃሉ
እነሆ ለሚያምኑበት ሁሉ
ቃልም ሥጋ ሆነና ፀጋን እውነት ተሞልቶ
በእኛ ዘንድ አደረ ክብሩን አየን ጐልቶ
በአባቱ እቅፍ ሆኖ አብን የተረከው
ቀድሞም የነበረው ቃል ወልድ ኢየሱስ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ