ደስ የሚለኝ
Des Yemilegn
2003 · ትራክ 3 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ደስ የሚለኝ ያኔ ብቻ ነው ያኔ
ስትከብር ስትነግስልኝ ምድህኔ
የምረካው ያኔ ብቻ ነው ያኔ
ከፍ ስትል ስትገንልኝ መድህኔ
ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ
በምስጋናህ ደስ ይለኛል
አንተን ማክበር ማሞጋገስ ያረካኛል (፪x)
ክበርልኝ የኔ ጌታ ክበርልኝ (፫x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ንገሥልኝ የኔ ወዳጅ ንገሥልኝ (፫x)
ሰው ሁሉ ገብቶት ሲያመሰግንህ
አምላኬ አንተ ነህ ጌታዬም ሲልህ
ሲዘመር ላንተ ሲሆን እልልታ
በሁሉም ስፍራ ስትሆን ጌታ
ያኔ ነው የኔ ደስታ ስትነግሥልኝ ጌታ (፪x)
ያኔ ነው የኔ ደስታ ስትከብርልኝ ጌታ (፪x)
አዝማች · Chorus
ደስ የሚለኝ ያኔ ብቻ ነው ያኔ
ስትከብር ስትነግስልኝ ምድህኔ
የምረካው ያኔ ብቻ ነው ያኔ
ከፍ ስትል ስትገንልኝ መድህኔ
ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ
በምስጋናህ ደስ ይለኛል
አንተን ማክበር ማሞጋገስ ያረካኛል (፪x)
ክበርልኝ የኔ ጌታ ክበርልኝ (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ንገስልኝ የኔ ወዳጅ ንገሥልኝ (፫x)
ሰው በፈቃዱ ሳይገደድ
ጌታን ሲከተል እርሱን ሲወድ
በቤቱም ሲኖር ሲቀር ተማርኮ
በፍቅሩ ጉልበት ሳይ ተንበርክኮ
ያኔ ነው ደስታዬኮ ሲበዛልህ አምልኮ (፬x)
አዝማች · Chorus
ደስ የሚለኝ ያኔ ብቻ ነው ያኔ
ስትከብር ስትነግስልኝ ምድህኔ
የምረካው ያኔ ብቻ ነው ያኔ
ከፍ ስትል ስትገንልኝ መድህኔ
ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ
በምስጋናህ ደስ ይለኛል
አንተን ማክበር ማሞጋገስ ያረካኛል (፪x)
ክበርልኝ የኔ ጌታ ክበርልኝ (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ንገስልኝ የኔ ወዳጅ ንገሥልኝ (፫x)
ፍጥረትም ካንተ ሥር ካንተ በታች
ሲሆን ሲገዛ ደግሞም ሲመች
በሥልጣንህ ቃል ታዞ ሲመራ
የገነነውን ስምህን ሲፈራ
ያኔ ነው የኔ ደስታ ስትነግሥልኝ ጌታ (፪x)
ያኔ ነው የኔ ደስታ ስትከብርልኝ ጌታ (፪x)
አዝማች · Chorus
ደስ የሚለኝ ያኔ ብቻ ነው ያኔ
ስትከብር ስትነግስልኝ ምድህኔ
የምረካው ያኔ ብቻ ነው ያኔ
ከፍ ስትል ስትገንልኝ መድህኔ
ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ
በምስጋናህ ደስ ይለኛል
አንተን ማክበር ማሞጋገስ ያረካኛል (፪x)
ክበርልኝ የኔ ጌታ ክበርልኝ (፫x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ንገስልኝ የኔ ወዳጅ ንገሥልኝ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ