መገረም
Megerem
2003 · ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
መገረም ገብቶበት ቃል እንደጠፋዉ
ቁጥር 1 · Verse 1
የልቤን ለመግለጽ ቋንቋ እንዳጠረዉ
በአሰራርህ ነፍሴ ተደንቃ ኖራለች
ምሥጋናው አንሶባት እንባን ታፈሳለች
ተባረክ ትልሃለች
ተመስገን ትልሃለች
ከፍ በል ትልሃለች
ነፍሴ እጅግ ወዳሃለች (፪x)
ከገመትኩትና ካሰብኩት በላይ
ማዳንህ ሲገለጥ ከላይ ከሰማይ
ሲደራረብብኝ ቸርነት ምህረትህ
የምለው ሲጠፋኝ አምላኬ በፊትህ
እንባ ቋንቋዬ ነው ይፍሰስ ከእግርህ ሥር
ያለኝን ምሥጋና ያውጣው ይናገር
ይገባሃልና የነፍሴ ስሜቷ
ባክህ ዝም አትበል ተቀበላት ጌታ
አዝማች · Chorus
መገረም ገብቶበት ቃል እንደጠፋዉ
ቁጥር 2 · Verse 2
የልቤን ለመግለጽ ቋንቋ እንዳጠረው
በአሰራርህ ነፍሴ ተደንቃ ኖራለች
ምሥጋናው አንሶባት እንባን ታፈሳለች
ተባረክ ትልሃለች
ተመስገን ትልሃለች
ከፍ በል ትልሃለች
ነፍሴ እጅግ ወዳሃለች (፪x)
እንዲሁ ተመስገን ብዬ የማላልፈው
ደግሞም በቋንቋዬ በቃል የማልገልጸው
በዘመኔ ሁሉ ከቶ ማልረሳው
አምላክ ቸርነትህ ለኔስ ብዙ ነው
አቤት አሰራርህ እጅግ ይደንቀኛል
መናገር ስጀምር እንባ ይቀድመኛል
ለማመስገን ቋንቋ ቃል አጥሮኛልና
በእንባዬ ላክብርህ ልውደቅ ልስገድና
አዝማች · Chorus
መገረም ገብቶበት ቃል እንደጠፋዉ
ቁጥር 3 · Verse 3
የልቤን ለመግለጽ ቋንቋ እንዳጠረው
በአሰራርህ ነፍሴ ተደንቃ ኖራለች
ምሥጋናው አንሶባት እንባን ታፈሳለች
ተባረክ ትልሃለች
ተመስገን ትልሃለች
ከፍ በል ትልሃለች
ነፍሴ እጅግ ወዳሃለች (፪x)
እግዚአብሔር አምላኬ ሆንከኝ ደስ ብሎኛል
ከዚህ በላይ ባርኮት ከቶ የት ይገኛል
አንተን ያገኘሁ ቀን ቤት ኑሮዬ ሞላ
ለዘመኔ ሁሉ ተገኘለት መላ
ምላሽ ባይሆነኝም ይህ የኔ ምሥጋና
ላደርግ የምችለው ይሄንን ነውና
ስለዚህ ተባረክ እላለሁ ከነፍሴ
የምወድህ ጌታ ኢየሱስ ንጉሤ
አዝማች · Chorus
መገረም ገብቶበት ቃል እንደጠፋዉ
ቁጥር 4 · Verse 4
የልቤን ለመግለጽ ቋንቋ እንዳጠረው
በአሰራርህ ነፍሴ ተደንቃ ኖራለች
ምሥጋናው አንሶባት እንባን ታፈሳለች
ተባረክ ትልሃለች
ተመስገን ትልሃለች
ከፍ በል ትልሃለች
ነፍሴ እጅግ ወዳሃለች (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ