ነፍሴ
Nefsie
2003 · ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከሰማይ የመጣው የውዴ ውብ ቃል
ልጄ ወዳጄ ሆይ አንቺ የኔ ሲል
በኮረብታዎች ላይ መጣልኝ ሲዘል
ሐዘኔን ሊያስረሳ ነፍሴን ሊያባብል (፪x)
አዝማች · Chorus
የነፍሴ የውስጤ የልቤ የሚገባው ወዳጄ
በቃሉ መጥቷል ወደ ደጄ
ሲያንኳኳ ከፍቼ የክብርን ንጉሥ አስገባለሁ
በአፉ ቃል ነፍሴን አጠግባለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ወዳጄ ሆይ ተነሽ ውበቴ ሆይ ነይ
ክረምቱም አለፈ ብቅ አትይም ወይ
አበቦች በምድር ይኸው ተገለጡ
ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውን ሰጡ
በዓለት ንቃቃት ያለሽ እርግብ ሆይ
ጊዜው ደርሷልና ነይ እንተያይ
እያለ ሲያጽናናኝ ወዳጄ በቃሉ
ነፍሴም ተነቃቃች እግሮቼም ዘለሉ
አዝማች · Chorus
የነፍሴ የውስጤ የልቤ የሚገባው ወዳጄ
በቃሉ መጥቷል ወደ ደጄ
ሲያንኳኳ ከፍቼ የክብርን ንጉሥ አስገባለሁ
በአፉ ቃል ነፍሴን አጠግባለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
የሥጋና የደሜን የልቤን ትርታ
የመንፈሴን ጩኸት የነፍሴን ሙግቷ
ከወንድም አልጦ እኔን ሚጠጋጋ
ወዳጅ አለኝና ለርሱ ብቻ ላውጋ
ዘልቆ የሚያረሰርስ ቃል አለና ባፉ
ሥሙን እየጠራሁ ልግባ ወደ እቅፉ
ቃል ብቻ ይናገር እኔም እሰማለሁ
ሸክሜን ሲያራግፈው ያኔ ሰው እሆናለሁ
አዝማች · Chorus
የነፍሴ የውስጤ የልቤ የሚገባው ወዳጄ
በቃሉ መጥቷል ወደ ደጄ
ሲያንኳኳ ከፍቼ የክብርን ንጉሥ አስገባለሁ
በአፉ ቃል ነፍሴን አጠግባለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ