Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እቅፍ ድግፍ

Eqef Degef

2003 · ትራክ 11 · 4:54 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እቅፍ ድግፍ እቅፍ በምክሩ ድግፍ

እቅፍ ድግፍ እቅፍ በቃሉ ድግፍ

አርጐ የሚመራ በዘመናት መሃል

እየሰባበረ ቅጥሩን የሚያዘልል

ማነው እንደ እግዚአብሔር አሃ

ማነው እንደ እግዚአብሔር እህ (፪x)

የአባትነት ፍቅር ምክሩ : ሳይለየኝ ማስተማሩ

ልክ እንደ ዓይን ብሌን : ተንከባክቧት ሕይወቴን (፪x)

እንዳልወድቅ እንዳልጠፋ : እየሰጠኝ ተስፋ

ይኸው አለሁኝ በቤቱ : እየዘመርኩ ምህረቱን (፪x)

እቅፍ ድግፍ እቅፍ በምክሩ ድግፍ

እቅፍ ድግፍ እቅፍ በቃሉ ድግፍ

አርጐ የሚመራ በዘመናት መሃል

እየሰባበረ ቅጥሩን የሚያዘልል

ማነው እንደ እግዚአብሔር አሃ

ማነው እንደ እግዚአብሔር እህ (፪x)

በጉያዎቹ ሸሽጐ : ከመከራው ቀን ታድጐ

ጠላቶቼ እንደጥላ : ቀሩና ወደ ኋላ (፪x)

ያንን ዘመን በእርሱ አልፌ : ከሞት ወጥመድ ተርፌ

ከክብር ጋር ዛሬን እንዳይ : ፈቀደልኝ ከሰማይ (፪x)

እቅፍ ድግፍ እቅፍ በምክሩ ድግፍ

እቅፍ ድግፍ እቅፍ በቃሉ ድግፍ

አርጐ የሚመራ በዘመናት መሃል

እየሰባበረ ቅጥሩን የሚያዘልል

ማነው እንደ እግዚአብሔር አሃ

ማነው እንደ እግዚአብሔር እህ (፪x)

በሃሩሩ በበረሃ : አፍለቅልቆ ከአለት ውኃ

የመላእክትን መና : ከሰማይ ያወርድና (፪x)

በእሳት አምድ በደመና : ከፊት ፊት ይመራና

ወደ ተስፋይቱ ምድር : ያደርሰኛል በክብር (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ