በግራና በቀኝ
Begrana Beqegn
2003 · ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በግራና በቀኜ ሆናችሁ
ልታጠምዱኝ ያሰፈሰፋችሁ
በሉ ስሙኝ እስቲ ልንገራችሁ
በእኔ ዘንድ ደግሞ ምን ቀራችሁ
አትጠጉኝ አትነካኩኝ
ተለያየን እኔ የጌታ ነኝ
በዓለም ብኖር አይደለሁ የዓለም
መኖሪያዬ ለዘልዓለም
በዚህች ምድር ፍጹም አይደለም
በዚህች ዓለም ፍጹም አይደለም (፪x)
አዝማች · Chorus
(አሃ) ዓይኖቼን አንስቼ (አሃ) ሳይ ወደ ሰማይ
(አሃ) በአብ ቤት ቁጭ ያለው (አሃ) በዙፋኑ ላይ
(አሃ) ተስፋውን የሰጠኝ (አሃ) መጥቶ ሊወስደኝ
(አሃ) የዘላለም አባት (አሃ) ኢየሱስ አለኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
የአምላክ ምክር የልዑል ትምህርቱ
የሰማሁት አዋጅ የመንግሥቱ
ውስጤ ገብቶ ሰርፆ ልቦናዬ
አጣብቆኛል ከውዱ ጌታዬ
ጊዜም የለኝ ዓለም ምሰማሽ
እረሳሁሽ አንቺም እኔን እርሺኝ
በአምላኬ ዘንድ ተሰራልኝ ቤቴ
ሰማያዊ ሆኗል ዜግነቴ (፭x)
አዝማች · Chorus
(አሃ) ዓይኖቼን አንስቼ (አሃ) ሳይ ወደ ሰማይ
(አሃ) በአብ ቤት ቁጭ ያለው (አሃ) በዙፋኑ ላይ
(አሃ) ተስፋውን የሰጠኝ (አሃ) መጥቶ ሊወስደኝ
(አሃ) የዘላለም አባት (አሃ) ኢየሱስ አለኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
በዚህ ምድር ቋሚ ነገር የለም
ምስቅልቅል ነው ሲኖር በዚህ ዓለም
የከበረ ነገ ይዋረዳል
ያለቀሰ በተራው ይስቃል
ግራ ገብቶት ሰው ሁሉ ሲሰጋ
የማምለጫው መንገዱ ሲዘጋ
ጌታዬና አምላኬ ነህ ብዬው
የእንግድነት ኑሮ ጀምሬያለሁ
አገር አለኝ ቤቴ በሰማይ ነው
ተስፋ አለኝ ርስቴ በሰማይ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
(አሃ) ዓይኖቼን አንስቼ (አሃ) ሳይ ወደ ሰማይ
(አሃ) በአብ ቤት ቁጭ ያለው (አሃ) በዙፋኑ ላይ
(አሃ) ተስፋውን የሰጠኝ (አሃ) መጥቶ ሊወስደኝ
(አሃ) የዘላለም አባት (አሃ) ኢየሱስ አለኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
የሰው ዕድሜ መች ከሰባው ያልፋል
ቢበረታ ሰማንያ ይሆናል
ጥቂት ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ
እንፋሎት ነው የኛ መኖር ተስፋ
እኔ ግን መች በምድር እቀራለሁ
በሰማይ ቤት መኖሪያ አግኝቻለሁ
ጌታ የግል አዳኜ ሆኖኛል
በብርሃኑ ብርሃን ወጥቶልኛል
የዘላለም ሕይወት ተሰጥቶኛል
የፍርድ ቀን ለምን ያሰጋኛል (፪x)
አዝማች · Chorus
(አሃ) ዓይኖቼን አንስቼ (አሃ) ሳይ ወደ ሰማይ
(አሃ) በአብ ቤት ቁጭ ያለው (አሃ) በዙፋኑ ላይ
(አሃ) ተስፋውን የሰጠኝ (አሃ) መጥቶ ሊወስደኝ
(አሃ) የዘላለም አባት (አሃ) ኢየሱስ አለኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ