Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በኪሩቤል ላይ

Bekirubel Lay

2010 · ትራክ 9 · 4:21 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከሰማያት በላይ በክብር ላለኸው

ለሞትና ለሲዖል ኃይልህን ያስታወቅከው

የዘላለም ደጆች ላንተ ይከፈቱ

የጽድቅ ንጉሥ ግባ ዛሬም እንደ ጥንቱ

በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ

የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ አንተ ታይ

በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ

የሰላም አለቃ ኢየሱስ አንተ ና

እንደተስፋ ቃልህ መጣህ ወደ ምድር

ለገባው ሚስጥሩ ታየ የአንተ ክብር

የማይሻር የጸና የትንቢት ቃል ይዘን

እስክትመጣ ኢየሱስ እንጠብቅሃለን

በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ

የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ አንተ ታይ

በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ

የሰላም አለቃ ኢየሱስ አንተ ና

ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) ሃሌሉያ (ሃሌሉያ)

በምሥጋና (በምሥጋና) እናንግሠው (እናንግሠው)

በኪሩቤል ላይ (በኪሩቤል ላይ) የምትቀመጥ

የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ አንተ ታይ

በኪሩቤል ላይ (በኪሩቤል ላይ) የምትቀመጥ

የሰላም አለቃ ኢየሱስ አንተ ና (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ