በሚመራኝ እሄዳለሁ
Bemimeragn Ehiedalew
2010 · ትራክ 2 · 6:09 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በሚመራኝ እሄዳለሁ
ህይወቴን ሰጥቼዋለሁ
አልረሳም አስታዉሳለሁ
በሞቱ ተፈውሻለሁ
አዝማች · Chorus
በሌት በቀኔ ይመራኛል
ኢየሱስ ያስፈልገኛል
እውነተኛ ወዳጄ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ነፍሴን በደሙ የገዛው
ትዕዛዝህን አከብራለሁ
በክንድህ እደገፋለሁ
ተስፋ ሳልቆርጥ እጓዛለሁ
አንድ ቀን አዳኜን አየዋለሁ
አዝማች · Chorus
በሌት በቀኔ ይመራኛል
ኢየሱስ ያስፈልገኛል
እውነተኛ ወዳጄ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
ነፍሴን በደሙ የገዛት
አልተክዝም ከቶ አልፈራም
አንተ ካለህ ከእኔ ጋራ
ፍጹም ፍቅርህ መድኃኒቴ
ማጽናኛ ነው ለሕይወቴ
አዝማች · Chorus
በሌት በቀኔ ይመራኛል
ኢየሱስ ያስፈልገኛል
እውነተኛ ወዳጄ ነው
ቁጥር 4 · Verse 4
ነፍሴን በደሙ የገዛት
አንዳንድ ጊዜ ፈተና ሲበዛ
መከራ ችግር ቢበዛብን
(ኧረ) አንድ እንኳ ቢታጣ የሚረዳ
ኢየሱስ አለ ከእኛ ጋራ
አንዳንድ ጊዜ ፈተና ሲበዛ (ሃሌሉያ)
መከራ ችግር ቢበዛብን
አንድ እንኳ ቢታጣ የሚረዳ (ቢታጣ)
ኢየሱስ አለ ከእኔ ጋራ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ