ላመስግነው አምላኬን
Lamesgenew Amlakien
2010 · ትራክ 6 · 5:41 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምድርና ሞላዋን በቃልህ ያፀናህ
በክብርህ ሞገስ በብርሃንህ ዓለምን የሞላህ
እንዴት ላክብርህ ዛሬስ ምን ይዤ በፊትህ ልግባ
አዲስ ምሥጋና አዲስ ዝማሬ አይበዛብህምና
አዝማች · Chorus
እጆቼን ወደ ሰማይ አንስቼ
በንጹህ ልብ ዛሬም እስከ ዘለዓለም
ላመስግነው አምላኬን በሰማይ ላለው
ለኢየሱስ ቅኔ ልቀኝለት (፪x)
ታማኝነቱንም ገናናነቱንም አይቼ
ቁጥር 2 · Verse 2
ስለ ምሕረትህ ባስብ ባወራ አመታት ያጥሩኛል
አቤቱ ኢየሱስ የታምራትህ ዘርፍ እረዝሟልና
ለነፍሴ ዘወትር ተሟግተሃል
ሕይወቴንም በደምህ ተቤዥተሃልና
አዝማች · Chorus
እጆቼን ወደ ሰማይ አንስቼ
በንጹህ ልብ ዛሬም እስከ ዘለዓለም
ላመስግነው አምላኬን በሰማይ ላለው
ለኢየሱስ ቅኔ ልቀኝለት (፬x)
ታማኝነቱንም ገናናነቱንም አይቼ
ቁጥር 3 · Verse 3
በላይ በዙፋንህ ላይ
በክብር ነግሰህ ታየህ አቤቱ (፬x)
(ክብር ይሁን)
ላመስግነው አምላኬን
በሰማይ ላለው ለኢየሱስ
ቅኔ ልቀኝለት (፪x)
በላይ በዙፋንህ ላይ
በክብር ነግሰህ ታየህ አቤቱ
(ክበር ክበር መድኃኒቴ)
በላይ በዙፋንህ ላይ
በክብር ነግሰህ ታየህ አቤቱ
(ክበር ንገሥ መድኃኒቴ)(፪x)
በላይ በዙፋንህ ላይ
በክብር ነግሰህ ታየህ አቤቱ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ