መድኃኒቴን አየዋለው
Medhanitien Ayewalew
2010 · ትራክ 3 · 6:07 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
መድኃኒቴን አየዋለሁ ዓይኖቼ ተከፍተዋል
በደሙና በስሙ ስላነጻን
ፍፁም ህይወት አሁን አለኝ በሞቱ ፈወሰኝ
አሮጌው ልማድ ከሕይወቴ ጠፍቷል
አዝማች · Chorus
አምላኬን ላመስግን ሥሙንም ልወድስ
ስላፈቀረኝ በመስቀል ተሰቅሎ (ሃሌሉያ)
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ኢየሱሴን ልወድስ
ለዓለም ህዝቦች የፍቅሩን ወንጌል ልግለጽ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ትኩስ ቀዝቃዛ ለብ ያለ ህይወት አትመኑ
የጌታ አገልጋይ እሳት ነበልባል ነው
በመንፈስ እሳት ግላቹህ እርሱን አገልግሉ
የድሉን አክሊል እንድትቀበሉ
አዝማች · Chorus
አምላኬን ላመስግን ሥሙንም ልወድስ
ስላፈቀረኝ በመስቀል ተሰቅሎ (ሃሌሉያ)
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ኢየሱሴን ልወድስ
ለዓለም ህዝቦች የፍቅሩን ወንጌል ልግለጽ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ነፍሴ አርፋለች በዙፋንህ ሥር
በጥላህ እታመናለሁ
መፍትሄ የሌለው ምንም ችግር
እንደማያገኘኝ አውቃለሁ
ከአንተ የተሻለ ጓደኛ የለኝም
ከአንተ የቀረበ ዘመድ አላገኝም
ከአንተ የበለጠ ምንም አልመኝም
ሆሆሆ ኢየሱስ አለልኝ ምንም አይጐለኝም (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ