የሕይወት ውኃ
Yehiwot Weha
2010 · ትራክ 4 · 5:13 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
"በዚያም በታላቁ ቀን ኢየሱስ ቆሞ
'ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ
በእኔ የሚያምን መጽሐፉ እንዳለው
የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል'
ዛሬም ይሄ ነው ፀሎታችን"
የእምነት ቃሉን የሰጠ እስከ ፍጻሜው ታማኝ ነው
የፍጥረት ሁሉ አባት ለልጆቹ የሚዋጋው
እሩህሩህ አምላኬ የፍቅር ውኃ ምንጭ
ኃጢአት እንዳይጥለኝ ያዝከኝ በቸርነት
አዝማች · Chorus
የሕይወት ውኃ ምንጭ የነፍስ ሁሉ እረኛ
ቁጥር 2 · Verse 2
ያንቀላፋው ልቤ በውሃው ይነሳል
አፍስስ ቅዱስ መንፈስህን ለተጠማች ነፍሴ
ይፍለቅ ፍቅርህ ከሕይወቴ ይህ ነው ፀሎቴ
ማንም የተጠማ ቢኖር ወደኔ ይምጣ ብለሃል
የሕይወት ውኃ ወንዝ በሰው ሁሉ ላይ ያድራል
የመንፈስ አንደበት የሰማያት እንባ
ፈሰሰ ከዓይኔ መቼም ላልጠማ
አዝማች · Chorus
የሕይወት ውኃ ምንጭ የነፍስ ሁሉ እረኛ
ቁጥር 3 · Verse 3
ያንቀላፋው ልቤ በውሃው ይነሳል (ማንም ለተጠማ የምትሰጥ እርካታ)
አፍስስ ቅዱስ መንፈስህን ለተጠማች ነፍሴ
ይፍለቅ ፍቅርህ ከሕይወቴ ይህ ነው ፀሎቴ
የሕይወት ውኃ ምንጭ በውኃው ይነሳል
አፍስስ ቅዱስ መንፈስህን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ