ዘመናት አይለውጡህም
Zemenat Aylewetuhem
2010 · ትራክ 5 · 4:51 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዘምን በዘመን ሲፈራረቅ
ቀኑም ለቀኑ ቦታም ቢለቅ
በዓመታት መሃል በቀናት ቁጥር
ከፍ ከፍ እያልክ የምትከብር (፪x)
የጊዜ ኃይል አይለውጥህም
አንተ ህያው ነህ አትቀየርም
ሚመስልህ የለም የሚገዳደርም
ማነው ኃይልህን የሚከለክልህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዘመናት አይለውጡህም ዓመታት አይሽሩህም
ቁጥር 3 · Verse 3
ቀናት አይቀይሩህም አንተ ሁሌ አንተ ነህ
ኢየሱስ ነህ አንተ አልፋ ኢየሱስ አንተ ኦሜጋ
ኢየሱስ ለዘለዓለም ኢየሱስ የሚመስልህ የለም
ቢፈራረቁ ክረምት ከበጋ
አንተ ግን ያው ነህ አልፋ ኦሜጋ
ጊዜው ሲገሰግስ እንደ ሰረገላ
አንተ አታረጅም አትቀርም ኋላ (፪x)
ሁሉ ፈጥረሃል በስልጣንህ
ተከናወነ በይሁን ቃልህ
በዙፋንህ ላይ ስንት ነዋሪ
አቻ የለህም ተወዳዳሪ ተገዳዳሪ
አዝማች · Chorus
ዘመናት አይለውጡህም አመታት አይሽሩህም
ቀናት አይቀይሩህም አንተ ሁሌ አንተ ነህ
ኢየሱስ ነህ አንተ አልፋ ኢየሱስ አንተ ኦሜጋ
ቁጥር 4 · Verse 4
ኢየሱስ ለዘለዓለም ኢየሱስ የሚመስልህ የለም (የሚመስልህ የለም)
የጥንቱ ክንድህ ይሰራል ዛሬም
ግሩም ችሎታህ አልተቀየረም
አንተ አትሻር አትለወጥም
ኢየሱስ ህያው ነህ ለዘለዓለም (፪x)
በሙሴ ዘመን ባህሩን ከፍለህ
በሐዋርያት ማዕበሉን ገሰጽክ
ብዙ ሰርተሃል በየዘመናት
እጅግ ድንቅ ነው የአንተ ተዓምራት
አዝማች · Chorus
ዘመናት አይለውጡህም አመታት አይሽሩህም
ቀናት አይቀይሩህም አንተ ሁሌ አንተ ነህ
ኢየሱስ ነህ አንተ አልፋ ኢየሱስ አንተ ኦሜጋ
ቁጥር 5 · Verse 5
ኢየሱስ ለዘለዓለም ኢየሱስ የሚመስልህ የለም (፪x)
ዘመናት አይለውጡህም አመታት አይሽሩህም
ቀናት አይቀይሩህም አንተ ሁሌ አንተ ነህ
ኢየሱስ ነህ አንተ አልፋ ኢየሱስ አንተ ኦሜጋ
ኢየሱስ ለዘለዓለም ኢየሱስ የሚመስልህ የለም (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ