ደስ ይለኛል
Des Yelegnal
1998 · ትራክ 4 · 5:22 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እኔስ በጌታዬ ደስ ይለኛል
ሕይወት ከእርሱ ጋራ ተስማምቶኛል
ካቻ አምናን በድል አሻግሮኛል
አምናንም በክንዱ ደግፎኛል
አሁንም ከክብር ወደ ክብር ያሸጋግረኛል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ጠመዝማዛው መንገድ ዳገት ቁልቁለቱ
ሕይወት ውጣ ውረድ ሲሆን በየዕለቱ
በሚያፀናው ክንዱ በኃይሉ ደግፎኝ
ቆምኩኝ በምሥጋና በእርሱ ደስ እያለኝ
አዝማች · Chorus
እኔስ በጌታዬ ደስ ይለኛል
ሕይወት ከእርሱ ጋራ ተስማምቶኛል
ካቻ አምናን በድል አሻግሮኛል
አምናንም በክንዱ ደግፎኛል
አሁንም ከክብር ወደ ክብር ያሸጋግረኛል
ቁጥር 2 · Verse 2
በዚያ ምድረበዳ ሀሩር በበዛበት
መናን እያበላህ እኔን የመራበት
ከአለቱ ውኃ አፍልቆ ያጠጣኝ
እንዴት ይረሳኛል ጌታ ያረገልኝ
አዝማች · Chorus
እኔስ በጌታዬ ደስ ይለኛል
ሕይወት ከእርሱ ጋራ ተስማምቶኛል
ካቻ አምናን በድል አሻግሮኛል
አምናንም በክንዱ ደግፎኛል
አሁንም ከክብር ወደ ክብር ያሸጋግረኛል
ቁጥር 3 · Verse 3
በለመለመው መስክ የሚያሳድረኝ
በእረፍት ውኃ ዘንድ ሁሌ የሚመራኝ
መልካም እረኛ ነው የሚያሳጣኝ የለም
ጌታ ተስማማቶኛል ከቶ አይሰለችም
አዝማች · Chorus
እኔስ በጌታዬ ደስ ይለኛል
ሕይወት ከእርሱ ጋራ ተስማምቶኛል
ካቻ አምናን በድል አሻግሮኛል
አምናንም በክንዱ ደግፎኛል
አሁንም ከክብር ወደ ክብር ያሸጋግረኛል
ቁጥር 4 · Verse 4
በውጊያ ዘመኔ ያራመደኝ በድል
የጠላቴን እራስ ያስረገጠኝ ልዑል
ከክበር ወደ ክብር ያሸጋግረኛል
አዲስ ነገር ሲያደርግ ዛሬም ያሳየኛል
አዝማች · Chorus
እኔስ በጌታዬ ደስ ይለኛል
ሕይወት ከእርሱ ጋራ ተስማምቶኛል
ካቻ አምናን በድል አሻግሮኛል
አምናንም በክንዱ ደግፎኛል
አሁንም ከክብር ወደ ክብር ያሸጋግረኛል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ