Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የምሥራች

Yemeserach

1998 · ትራክ 13 · 4:33 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

(የምስራች የምስራች ይኸው

የምስራቹ ጽዮን ደርሰናል አትሰልቹ

ያቻት ባሻገር የጻድቃኖች አገር) (፪x)

ዘመናት ቆጥረን እዚህ ደርሰናል

እንግዲህ : ልናርፍ ሰዓቱ ደርሷል

ከተራራው ጐን የምትታየው

ጽዮን ያች ናት ድንቋ ቤታችን

የምስራች

ቅጥሯን ልንረግጥ ምንም አልቀረን

እፎይ ለማለት ጽዮን ቤታችን

ከማዶ ያለው የአትክልት ቦታ

የጽዮን ቤት ነው የሰጠን ጌታ

የምስራች

ተራራ ጋርዶን ሳናያት ነበር

አሁን ምን ቀረን ከጽዮን ቤት

አቤት ማማሩ አበባው መስኩ

ግምቴ ይሄ ነው የውበት ልኩ

የምስራች

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ