Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ለዚህ ነው መቆሜ

Lezih New Meqomie

1998 · ትራክ 3 · 3:06 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አላማ ቢስ ነበርኩ ግብ የሌለሽ

የማልረባ ብኩን ተቅበዝባዥ

ኢየሱስ ግን ውስጤ ገባ

ድፍርስ ሕይወቴን አጠራ

መራራው ሕይወቴ ተለወጠ

ኑሮዬ በኢየሱስ ጣፈጠ

(ለዚህ ነው መቆሜ በደስታ መዘመሬ

በቅኔ ውዳሴ ወደሱ መቅረቤ) (፪x)

ሁሉ ግራ ገብቶኝ ብዙ ባከንኩ

የሚያረካኝ ጠፍቶ ታወኩኝ

ኢየሱስ ግን ሕይወት ሰጠኝ

ዳግም ላልጠማ አረካኝ

የመዳኔን ምስራች ስሰማ

ልቤ ቀለጠ እንደ ሻማ

ለዚህ ነው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ