Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጥሪ አለው ለአንተ

Teri Alew Lante

1998 · ትራክ 7 · 3:17 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጥሪ አለው ለአንተ ጌታ ኢየሱስ

ፊትህን ወደ እርሱ እንድትመልስ (፪x)

በዓለም መኖርህ የታል ደስታው

ነፍስህ እረፍትን መቼ አይታው

ተው ልብ ብለህ ስማኝ ወንድም

ምን ፍሬ አገኘህ ከዚህ ዓለም (፪x)

ጥሪ አለው ለአንተ ጌታ ኢየሱስ

ፊትህን ወደ እርሱ እንድትመልስ (፪x)

ሰላም አለኝ ብትል ትዋሻለህ

ደስታ አለኝ ብትል ትቀጥፋለህ

ከጌታ እርቆ እረፍት የለም

ውስጥህ ያውጠንጥነው ተው ግድ የለም (፪x)

ጥሪ አለው ለአንተ ጌታ ኢየሱስ

ፊትህን ወደ እርሱ እንድትመልስ (፪x)

ብትጠላው እንኳን ያፈቅርሃል

ክፋትህን እንዲያይ መች ይወዳል

ፊትህን አዙረህ ብትሸሸው

እጁ እስኪያገባህ ትዕግስት አለው (፪x)

ጥሪ አለው ለአንተ ጌታ ኢየሱስ

ፊትህን ወደ እርሱ እንድትመልስ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ