Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እናከብርሃለን

Enakebrehalen

1998 · ትራክ 5 · 5:05 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እናከብርሃለን እናነግስሃለን

ውለታህ ብዙ ነው ኢየሱስ

ማዳንህም ለዘላለም

ሥራህ ድንቅ ነው ተዓምር

ይገባሃል ዛሬም ክበር (፪x)

በኃጢአት ወድቀን ወንጌል ሰበክልን

አሮጌውን ሕይወት በአዲስ ለወጥክልን

ቀንበራችን ሰብረህ ነጻ አወጣኸን

የናዝሬቱ ኢየሱስ ከብረህ አከበርከን

እናከብርሃለን እናነግስሃለን

ውለታህ ብዙ ነው ኢየሱስ

ማዳንህም ለዘላለም

ሥራህ ድንቅ ነው ተዓምር

ይገባሃል ዛሬም ክበር

ስጦታ ስትሰጥ እጆችህ መሉዎች

በመንፈስ በፀጋ በክብር ታላቆች

በአደባባዮችህ ሰንቆም በምሥጋና

ከዓመታት መካከል ክበር እንደገና

እናከብርሃለን እናነግስሃለን

ውለታህ ብዙ ነው ኢየሱስ

ማዳንህም ለዘላለም

ሥራህ ድንቅ ነው ተዓምር

ይገባሃል ዛሬም ክበር

በሞገስ በክብር በግርማ ያለኸው

ልዑል ዙፋንህን ማንም የማይሽረው

ሥጋና ነፍሳችን መንፈሳችን ሁሉ

በእውነትና በመንፈስ ለአንተ ይገዛሉ

እናከብርሃለን እናነግስሃለን

ውለታህ ብዙ ነው ኢየሱስ

ማዳንህም ለዘላለም

ሥራህ ድንቅ ነው ተዓምር

ይገባሃል ዛሬም ክበር

ዛሬም በምድር ላይ ሰላምን ሰጥተኽን

በሰማዩ ስፍራ በቀኝ አስቀመጥከን

በዚህ ሳንወሰን ጽዮን እንገባለን

ለዘለዓለም በፍትህ እንዘምራለን

እናከብርሃለን እናነግስሃለን

ውለታህ ብዙ ነው ኢየሱስ

ማዳንህም ለዘላለም

ሥራህ ድንቅ ነው ተዓምር

ይገባሃል ዛሬም ክበር (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ