Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሃሌሉያ

Hallelujah

1998 · ትራክ 6 · 3:19 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ገና ተጓዝ ነኝ የሩቅ አገር ሰው

በጌታዬ ቤት ስደርስ የማልፈው

በጉን በግርማ ፊት ለፊት ሳየው

በዚያ እኖራለሁ ሆኜ አዲስ ሰው

እስከዚያች ቀን ግን በጣም እተጋለሁ

መከራም ቢኖር በሥሙ አልፋለሁ

ሃሌሉያ ምን ይሳንሃል

ሃሌሉያ ሁሉን ችለሃል

ሃሌሉያ ዮርዳኖስንም

ሃሌሉያ ክንድህ ከፈለው

ማዕበሉን ደግሞ ቃልህ አዘዘው

ብደክም ብዝል ብወድቅ ብነሳ

ስማቅቅ ብኖር ከእርሱ አልለይም

የአሁን ክሳቴ ጉስቁልናዬ

ሁሉም አይኖርም ሳገኝ ጌታዬን

አንድ ቀን ከጽዮን ድምጹን ስሰማ

እበረታለሁ ሁሉም ያልፍና

ሃሌሉያ ምን ይሳንሃል

ሃሌሉያ ሁሉን ችለሃል

ሃሌሉያ ዮርዳኖስንም

ሃሌሉያ ክንድህ ከፈለው

ማዕበሉን ደግሞ ቃልህ አዘዘው

ትላንት ተዋግቶ ነፍሴን ካዳናት

ዛሬ የሚታክት አምላክ መች አላት

አይለወጥም ዛሬም ኃያል ነው

በእውነት አምላኬ የድል ጌታ ነው

ስለዚህ ጠላት ተስፋህ ይደምሰስ

ነው መሠረቴ አለት የማይፈርስ

ሃሌሉያ ምን ይሳንሃል

ሃሌሉያ ሁሉን ችለሃል

ሃሌሉያ ዮርዳኖስንም

ሃሌሉያ ክንድህ ከፈለው

ማዕበሉን ደግሞ ቃልህ አዘዘው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ