እዘምራለሁ
Ezemralehu
1998 · ትራክ 8 · 4:29 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ምህረቱን ቸርነቱን
እዘምራለሁ እንዴት ዝም ልል እችላለሁ
እዘምራለሁ እጅግ ፈሶልኝ አይቻለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አብዝቼ ልወደው በእርግጥ ይገባኛል
ብዙ የነበረው ኃጢአቴ ተፍቋል
ዝቅ ብዬ እግሮቹን በእምባዬ ላርሰው
ብልቃቱም ይሰበር ሽቶውን ላፍስሰው (፪x)
አዝማች · Chorus
ምህረቱን ቸርነቱን
እዘምራለሁ እንዴት ዝም ልል እችላለሁ
እዘምራለሁ እጅግ ፈሶልኝ አይቻለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
የኃጢአተኛ ወዳጅ ስለ እኔ ተባለ
ዘኪዮስ ሆይ ቤትህ ውላለው ስላለ
ዛሬ ቀን ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል
ብሎ መድኃኒቴ ምህረትን አውጇል (፪x)
አዝማች · Chorus
ምህረቱን ቸርነቱን
እዘምራለሁ እንዴት ዝም ልል እችላለሁ
እዘምራለሁ እጅግ ፈሶልኝ አይቻለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
ምህረቱ ያዘኝ ከቤቱ እንዳልወጣ
ቸርነቱ በዛ አንዳች እንዳላጣ
በሕይወቴ ዘመን እያተከተሉኝ
አምላኬ ከአንተ ጋር በቤትህ አኖሩኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምህረቱን ቸርነቱን
እዘምራለሁ እንዴት ዝም ልል እችላለሁ
እዘምራለሁ እጅግ ፈሶልኝ አይቻለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ