እንዳንተ ማንም የለም
Endante Manem Yelem
1998 · ትራክ 9 · 5:33 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እንዳንተ ማንም የለም እንዳንተ ማን
እንዳንተ ማንም የለም መድኃኒት ለዓለም
ኢየሱስ ካለ አንተ የለም (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
መሄጃ ለጠፋው ግራ ለገባው ሰው
የኃጢአት ቀንበር ከብዶት ሸክም ለተጫነው
ወደ እኔ ይምጣና አሳርፈዋለሁ
የሚል ጌታዬ ሆይ ከአንተ በቀር ማነው
አዝማች · Chorus
እንዳንተ ማንም የለም እንዳንተ ማን
እንዳንተ ማንም የለም መድኃኒት ለዓለም
ኢየሱስ ካለ አንተ የለም
ቁጥር 2 · Verse 2
ልከፍለው የማልቻል ዕዳ ተሸክሜ
በዘላለም ደዌ በኃጢአት ታምሜ
በጐልጐታ መስቀል ዕዳዬን ከፍለሃል
እንዳንተ ያለ ወዳጅ ኧረ የት ይገኛል
አዝማች · Chorus
እንዳንተ ማንም የለም እንዳንተ ማን
እንዳንተ ማንም የለም መድኃኒት ለዓለም
ኢየሱስ ካለ አንተ የለም
ቁጥር 3 · Verse 3
ኃጢአተኛ ብሎ ሰው ሲፈርድባት
በድንጋይ ውግራት ሞት ተወስኖባት
አንተ ግን በምህረት ፍርዷን ለወጥከና
ነጻ ሰው አደረካት ለሥምህ መሥጋና
አዝማች · Chorus
እንዳንተ ማንም የለም እንዳንተ ማን
እንዳንተ ማንም የለም መድኃኒት ለዓለም
ኢየሱስ ካለ አንተ የለም
ቁጥር 4 · Verse 4
ለብዙ ዘመናት ከአልጋ ተቆራኝቶ
ወደ መጠመቂያው የሚያስገባው አጥቶ
ረዳትና አጋዥ ወገን ለሌለው ሰው
አንተ ነህ ኢየሱስ ፈጥነህ የደረስከው
አዝማች · Chorus
እንዳንተ ማንም የለም እንዳንተ ማን
እንዳንተ ማንም የለም መድኃኒት ለዓለም
ኢየሱስ ካለ አንተ የለም
ቁጥር 5 · Verse 5
ከነገድ ከቋንቋ ሕዝቦችን ልትዋጅ
የአምላካችን መንግሥት ቃላት ልታዘጋጅ
ስለ ኃጢአታችን እንደ በግ ታርደሃል
በረከት ምሥጋና ክብርም ይገባሃል
አዝማች · Chorus
እንዳንተ ማንም የለም እንዳንተ ማን
እንዳንተ ማንም የለም መድኃኒት ለዓለም
ኢየሱስ ካለ አንተ የለም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ