እግዚአብሔር በከፍታው
Egziabhier Bekefetaw
1998 · ትራክ 7 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር በከፍታው ድንቅ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ድንቅ ነው
ቁጥር 1 · Verse 1
፩) ፈርኦን ሊገዛ እስራኤልን
ልቡን አደንድኖ ከፍ ቢልም
ሕዝቡን ለመታደግ የቆረጠው
የሰራዊት ጌታ አሸነፈው
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር በከፍታው ድንቅ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ድንቅ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
፪) ዳንኤል ቢጣልም በጉድጓዱ
አንበሳ እንዲበላው ቢታዘዝ
የኃያላን ሀያል ኢየሱስ
አዳነ ካንበሳው ባሪያውን
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር በከፍታው ድንቅ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ድንቅ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
፫) መከራ ቢከበን ዙሪያችን
ተቆረጠ ስንል ተስፋችን
በከፍታዎች ላይ ከፍ የሚል
ልዑል አምላካችን ባለድል
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር በከፍታው ድንቅ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ድንቅ ነው
ቁጥር 4 · Verse 4
፬) አይሆንም ተብሎ ተቆርጦ
ተስፋዬ በሙሉ ተሟጦ
እግዚአብሔር ቃሉን አሰበ
ነገር በጊዜው ጨኮለ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር በከፍታው ድንቅ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ድንቅ ነው
ቁጥር 5 · Verse 5
፭) አፍ ባለው ነገር ላይ ከፍ ብሎ
በከፍታዎች ላይ ድንቅ ሆኖ
የኖረ ሳይረታ ዘላለም
እግዚአብሔርን የሚመስል የለም
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር በከፍታው ድንቅ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ድንቅ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ