አምልኮዬ
Amlekoyie
1998 · ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በወሬ አይደለም እኛ የሰማነው
በሕይወታችን እልፍ ጌታ አደረገው
ልዩ አፍቃሪ ወዳጅ አባት እግኝተናል
ልናመልክ ልንሰግድ በፊቱ ወጥተናል
ላምልከው እያልኩኝ እወደዋለሁኝ
የመስቀሉን ሚስጥር ፍቅር እያየሁኝ
ውለታው ስለእኔ እጅግ በዝቶልናል
እኔ አበዛለሁ ለሥሙ ምስጋና
እርሱ ብቻ አምላክ አባት ሆኖአልና
ይገባል ለስሙ አምልኮ ምሥጋና
አዝማች · Chorus
ስጡት ከልባችሁ አብዙለት ዘምሩ
ብቻውን ይመለክ ይወራለት ክብሩ
የተነሱበትን ጥሎ አዋረዳቸው
ሥልጣኑን ቀምቶ ባዶ አደረጋቸው
እነማን በርትተው እግዚአብሔርን ሻሩ
እርሱ እኮ ይኖራል በነበረ ክብሩ
ሥልጣኑ እጅግ ትልቅ ነው
ፈቅጄ እመልከዋለሁ
ወድጄ እምበረከካለሁ
ልናገር ከምችለው በላይ
ትልቅ ነው የክንዱ ሥልጣን
ገብቶኛል እዘምራለሁ
ሥልጣኑ ከማንም በላይ ነው
ስልጣኑ
ቁጥር 2 · Verse 2
ኃያል ነን ጐበዝ ነን እያሉ
በእርሱ ላይ ብዙ ፎረኩ
ታገሰ ዘመን ሰጣቸው
ታበዩ ክንዱ አጠፋቸው
በዘመኑ በታሪክ የለም
ስላጣኑ ፍፁም አልተሻረም
እንዴት ልናወጥ እንዴትስ ልፍራ
እያየሁ የክንዱን ስራ
ተደላድዬ ቆሜያለሁ
ኃያሉን ክንዱን ይዣለሁ
ሊሰራ እርሱ ሲነሳ
እያየሁ ሁሉም ይታዘዛል
ስልጣኑ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ