ያለፍነውን
Yalefnewen
1998 · ትራክ 4 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ያለፍነውን ያሳለፈን አረማነው
ዮርዳኖስን የከፈለው አረ ማነው
ማነው (፪x) አረማነው (፪x)
እግዚአብሔር ነው ብርቱ ሃያል
እግዚአብሔር ነው በሰልፍ ኃያል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
፩) ኃጢአታችን እጅግ በዝቶ
ነፍሳችንን አስጨንቆ
መንፈስ ቅዱስ በኛ አዝኖ
ሀይወታችን ተበላሽቶ
የተቤዥን በምህረቱ ያስታረቀን ከአባቱ
የዘላለም ጠባቂያችን ኢየሱስ ነው እረኛችን
እንደ እግዚአብሄር ለዘላለም
የሚችለን ማንም የለም
ቁጥር 2 · Verse 2
፪) በባዕድ ምድር ስንጨቆን
ስንገዛ በፈርኦን
መከራችን የተሰማው
ሃዘናችን ያሳዘነው
እስራትን የሰበረ ቀንበሩንም የሰበረ
ባለድሎች ያደረገን መልካም ነገር ያጠገበን
እንደ እግዚአብሔር ለዘላለም
የሚረዳን ማንም የለም
ቁጥር 3 · Verse 3
፫) የእኛን መውደቅ የተመኙ
ጉድጓዳችንን የቆፈሩ
በእጃቸው ተንኮል ይዘው
ወጥመዶችን ለእኛ አጥምደው
ዛሬ ነገ ጠፋ ያለ የኛን ረዳት ያላወቁ
እጃቸውን በአፋቸው አድርገዋል በስራቸው
እንደ እግዚአብሔር ለዘላለም
የሚያጸናን ማንም የለም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ