የመከራው ዘመን
Yemekeraw Zemen
1998 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የመከራው ዘመን ሁሉ አለፈና
ኢየሱስ ልዩ ነው አልን እንደገና
ሃሌሉያ እሰይ አሜን አሜን አልን
አዝማች · Chorus
ኢየሱስን ይዘን አሸናፊ ሆንን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከቁጣው ጢስ ወጣ ፍርድ ከርሱ በራ
አሳትም ነደደ ከሰማይ ወጣና
በኪሩቤል ሆኖ በፍጥነት በረረ
የጠላቴን ሰፈር ገባ እየሰበረ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ፍላጻውን ላከ ሁሉን በተናቸው
በመብረቁ እሳት ጌታ አወካቸው
ቋጠሮውን ውሉን ጌታዬ ፈታታው
የፎከረን ጠላት መደበቂያ አሳጣው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ለወይኔ አጥር ጌታ ክብር ሆኖ
ጠላቴን በክንዱ በኃይሉ በትኖ
ይኸው ለዚህ እለት ልንበቃ ችለናል
መከራችን ሁሉ እንደጉም ተነስቷል/በኢየሱስ ተነስቷል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ