የተወጋ ጐኑን
Yetewega Gonun
1998 · ትራክ 5 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የተወጋ ጐኑን እጆቼ ሲነካ
እይኖቼ በሩልኝ ሕይወት አለው ለካ
እንደሞተ አልቀረም ኢየሱስ ተነስቷል
ለሞተው ነገሬ ሕያው ነፍስን ዘርቷል
ቁጥር 1 · Verse 1
፩) መቃብር አትሂዱ የሱስ በዚያ የለም
ሕያው ሆኗል እሱ ሕያው ለዘላለም
እጆቹን ነክቸ እኔ ፈውስ አገኘሁ
ስለዚህ ተነስቷል ተነስቷል እላለሁ
አዝማች · Chorus
የተወጋ ጐኑን እጆቼ ሲነካ
እይኖቼ በሩልኝ ሕይወት አለው ለካ
እንደሞተ አልቀረም ኢየሱስ ተነስቷል
ለሞተው ነገሬ ሕያው ነፍስን ዘርቷል
ቁጥር 2 · Verse 2
፪) ዐይኖቸ አይተውታል ኢየሱስ ተነስቷል
በልብ ጓዳዬ በኑሮዬ ገብቷል
አትፍራ ብሎ አለኝ ዳሰኝ ቅረብና
አዎ ሕያው ሆኗል ኢየሱስ እንደገና
አዝማች · Chorus
የተወጋ ጐኑን እጆቼ ሲነካ
እይኖቼ በሩልኝ ሕይወት አለው ለካ
እንደሞተ አልቀረም ኢየሱስ ተነስቷል
ለሞተው ነገሬ ሕያው ነፍስን ዘርቷል
ቁጥር 3 · Verse 3
፫) ዛሬስ አምሮበታል ባባቱ ቀኝ አለ
ሁሉን በመታዘዝ ስለተቀበለ
ከሥም ሁሉ በላይ ስምም ተሰጥቶታል
ፍጥረት ሁሉ የሱስ ጌታ ነህ ይሉታል
አዝማች · Chorus
የተወጋ ጐኑን እጆቼ ሲነካ
እይኖቼ በሩልኝ ሕይወት አለው ለካ
እንደሞተ አልቀረም ኢየሱስ ተነስቷል
ለሞተው ነገሬ ሕያው ነፍስን ዘርቷል
ቁጥር 4 · Verse 4
፬) ተስፋ እንደሌለው እንበታተንም
ሰብሳቢ ቃል አለው እኛ አንወድቅም
የሞተ የማይሰማ አምላክ አናመልክም
ይሰራል ተነስቷል ሕያው ነው ዘላለም
አዝማች · Chorus
የተወጋ ጐኑን እጆቼ ሲነካ
እይኖቼ በሩልኝ ሕይወት አለው ለካ
እንደሞተ አልቀረም ኢየሱስ ተነስቷል
ለሞተው ነገሬ ሕያው ነፍስን ዘርቷል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ